Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ ምግብ እና ምግብ ነክ ምርቶችን በመገበያያ ገንዘቧ ለውጭ ገበያ ማቅረብ ልትጀምር ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ ከነዳጅ ምርት በተጨማሪ ምግብ እና ምግብ ነክ ምርትችን በመገበያያ ገንዘቧ (ሩብል) ለውጭ ገበያ ማቅረብ እንደምትጀምር አስታወቀች ፡፡

የሩሲያ መንግስት ጥራጥሬ፣ ሱፍ፣ ዘይት እና የተቀነባበሩ ምግቦችን መግዛት የሚፈልጉ ሀገራት ክፍያቸውን በሩሲያ መገበያያ ገንዘብ (ሩብል) መክፈል እንደሚገባቸው አስታውቋል።

ለውሳኔው ተፈጻሚነት የሚረዳ የውሳኔ ሃሳብም በሀገሪቱ ህግ ተቀባይነት አግኝቶ ለትግበራ ዝግጅት ላይ ነው ተብሏል፡፡

የሩሲያ የግብርና ሚኒስትር ዲሚትሪ ፓትሩሼቭ÷ በዚህ ወር ሀገራቸው የግብርና ምርቶችን ወደ “ወዳጅ ሀገራት” ብቻ እንደምትልክ ተናግረዋል፡፡

የሩሲያ የእህል ምርት በዚህ አመት 130 ሚሊየን ቶን ሊደርስ እንደሚችል የተናገሩት ሚኒስትሩ ይህም የሀገር ውስጥ ፍላጎቶችን ለመሸፈን እና ወደውጭ ለምትልከው የግብርና ምርት የሚበቃ እንደሆነ መግለጻቸውን አርቲ ዘግቧል ፡፡

ሩሲያ በዓለም ትልቋ የስንዴ እና የሱፍ ምርት አቅራቢ መሆኗ ይታወቃል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.