Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ በምስራቃዊ ሱዳን የጦር ሰፈር ልትገነባ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 3፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ሩሲያ በምስራቃዊ ሱዳን የባህር ሃይል የጦር ሰፈር ልትገነባ መሆኑ እየተሰማ ነው፡፡

ሃገራቱ በፖርት ሱዳን የጦር ሰፈሩን መገንባት የሚያስችል ረቂቅ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

በረቂቅ ስምምነቱ መሰረትም ሩሲያ ኒውክሌር የመሸከም አቅም ያላቸውን አራት የጦር መርከቦች በጦር ሰፈሩ ማስፈር ትችላለች፡፡

ከዚህ ባለፈም 300 የባህር ሃይል አባላቷን በሱዳን ወደብ ላይ ማስፈር ትችላለችም ነው የተባለው፡፡

በረቂቁ ላይ ሩሲያ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን ለጦር ሰፈሯ ማቅረብ እንደምትችል ተገልጿል፡፡

እንዲሁም የምታስገባቸው ዕቃዎች ከፍተሻ ነጻ መሆናቸውንም ስምምነቱ ያትታል፡፡

ሩሲያ በምላሹ ሱዳን ለምታደርገው ጸረ ሽምቅ ውጊያ ሙያዊ ድጋፍ ታደርጋለች ተብሏል፡፡

ሞስኮ በፖርት ሱዳን ላይ የጦር መርከቦቿን ለማስፈር ያቀደችው ሌሎች ሃገራትን ለመውጋት ሳይሆን በቀጠናው ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን መሆኑን ነው የገለጸችው፡፡

ሃገራቱ በኦማር ሃሰን አልበሽር አስተዳደር ዘመን ለሰባት ዓመታት የሚቆይ ወታደራዊ ትብብር ስምምነት መድረሳቸው ይታወሳል፡፡

 

ምንጭ፦ ዘ ሞስኮ ታይምስ

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.