Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ በትግራይ ክልል የተጎዱ መሰረተ ልማቶችን ለመጠገን በሚደረገው ጥረት ድጋፍ እንደምታደርግ ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 23፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌት ተረኪን ሃገራቸው በትግራይ ክልል የተጎዱ መሰረተ ልማቶችን ወደ ስራ ለመመለስ በሚደረገው ጥረት ድጋፍ እንደምታደርግ አስታወቁ፡፡

አምባሳደሩ መንግስት በትግራይ ክልል ያካሄደውን ህግ የማስከበር እና የህልውና ዘመቻ ማጠናቀቁን በመልካም ጎኑ እንደሚያዩትም ገልጸዋል፡፡

በርካታ ንጹሃን ሰዎች ሳይጎዱ የህግ ማስከበር ዘመቻው በመጠናቀቁ ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል፡፡

በክልሉ ውድመት የደረሰባቸውን መሰረተ ልማቶች በተቻለ ፍጥነት ወደ ስራ እንዲገቡ ከኢትዮጵያ ጎን እንደሚቆሙም ነው የገለጹት፡፡

አምባሳደሩ በክልሉ የተወሰደው የህግ ማስከበር ዘመቻ ሀገራቸው የኢትዮጵያ ውስጥ ጉዳይ ነው ብላ እንደምታምንም አስረድተዋል፡፡

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.