Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ በኢትዮጵያ የሚደረገውን የመልሶ ማቋቋም ተግባር እንደምትደግፍ ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ በኢትዮጵያ በጦርነቱ ምክንያት የደረሰውን ጉዳትና ውድመት መልሶ ለማቋቋም የሚከናወኑ ተግባራትን ትደግፋለች ሲሉ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴሬክሂን ተናገሩ።
 
ድጋፍ ለማድርግ ይረዳ ዘንድም በጦርነቱ ምክንያት የደረሰውን ውድመትና በመሰረታዊነት የሚያስፈልጉ ነገሮችን ለማወቅ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ነው የገለጹት።
 
አምባሳደሩ በተለይም በመሰረተ ልማትና በተቋማት ላይ ከደረሰው ጉዳትና ውደመት አንጻር መልሶ ግንባታው ብዙ ጥረት ይፈልጋል ብለዋል።
 
“በዚህ ሂደት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ፣ የእኛ ድርሻ ምን መሆን እንዳለበትም እያሰብን ነው” ሲሉ ገልጸዋል።
 
እንድ አምባሳደሩ ገለጻ÷ የአገራቸው መንግስት ድጋፍ ለማድረግ በኢትዮጵያ መንግስት በኩል የተጠቃለለ የጉዳት ሪፖርት እስከሚወጣ ይጠብቃል።
በመቀጠልም የመልሶ ማቋቋም ስራው እንዴት መሆን እንዳለበትና የሩሲያ መንግስት ድርሻ ምን እንደሚሆን የመለየት ስራ ይሰራል ነው ያሉት።
 
ኢትዮጵያ የገጠማትን ችግር እንድትሻገር ተጨባጭና ተግባራዊ እንስቃሴ እንደሚደረግም አክለዋል።
 
ይህም ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ በሚፈልገው መልኩ ሕይወቱን እንዲመራ ሩሲያ ድጋፏን ትቀጥላለች ብለዋል።
 
የኢትዮጵያ ሕዝብ መብቱ ተከብሮለት የመረጠውንና የፈለገውን ሕይወት እንዲሁም ዕጣ ፈንታውን የመወሰን የራሱ መብት እንዲከበርለት ሩሲያ ትታገላለች ማለታቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡
አምባሳደሩ በኢትዮጵያና በሩሲያ መካከል ያለው ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ሠብዓዊ እንዲሁም የትምህርትና የጤና ዘርፍ ትብብር እያደገ መምጣቱንም አውስተዋል።
 
የአገራቱ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከምዕት ዓመት በላይ መሆኑን በመጥቀስም “ወደፊትም ራሺያ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ የሚደረገውን ጠልቃ ገብነት መቃወሟን ትቀጥላለች” ብለዋል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.