Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ አንካራ አዲስ ተዋጊ ጄት ለማምረት የምታደርገውን ጥረት ለማገዝ ዝግጁ መሆኗን አስታወቀች

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ አንካራ አዲሱን አምስተኛ ትውልድ ተዋጊ ጄት ለማምረት የምታደርገውን ጥረት ለማገዝ ዝግጁ መሆኗን አስታወቀች።

ሞስኮ የኔቶ አባል የሆነችውን ቱርክ አዲሱን ተዋጊ ጄት እንድታመርት ለመርዳት ዝግጁ መሆኗን የሩሲያ ወታደራዊ-ቴክኒካል ትብብር አገልግሎት ኃላፊ ዲሚትሪ ሹጋዬቭ ተናግረዋል።

በዚህ ፕሮጀክት ዙሪያም አሁን ላይ ሞስኮ ከአንካራ ጋር ድርድር ላይ መሆኗንም ገልጸዋል።

በቱርክ የመከላከያ ኢንዱስትሪዎች ሊቀመንበር ኢስማኤል ደሚር ባለፈው አንካራ በመሰል ተዋጊ ጄቶች ዲዛይን ዙሪያ ከወዳጅ አገራት ጋር በትብብር መስራት እንደምትፈልግ መግለጻቸውን አር ቲ በዘገባው አስታውሷል።

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በፈረንጆቹ 2019 የአምስተኛውን ትውልድ የሆነውንና ከራዳር እይታ ውጭ የሚበረውን ኤስ ዩ-57 ዘመናዊ ተዋጊ ጄለቱርኩ ፕሬዚዳንት ረጂፕ ጣይፕ ኤርዶኻን ማሳየታቸው የሚታወስ ነው።

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.