Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ እና ዩክሬን በቱርክ እንዲደራደሩ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ታይፕ ኤርዶኻን ጠየቁ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ታይፕ ኤርዶኻን ሩሲያ እና ዩክሬንን በኢስታንቡል ለማደራደር ዝግጁ መሆናቸውን አስታወቁ፡፡

ኤርዶኻን ሀገራቱ በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲደራደሩ ጥሪ ያቀረቡት በትናንትናው ዕለት ለሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በስልክ ባስተላለፉት መልዕክት ነው፡፡

ሁለቱ ሀገራት በሚያቀርቧቸው መርሆዎች ላይ ከተስማሙ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተወካዮች ጋር በመሆን በቱርክ ኢስታንቡል በሚያዘጋጁት ውይይት ሀገራቱን ለማደራደር ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።

ፕሬዚዳንት ኤርዶኻን ሁለቱ ሀገራት ምኅዳሩን ለሠላም ማመቻቸት እንዳለባቸው እና በመተማመን ላይ የተመሠረተ የተኩስ አቁም በማድረግ የጦርነቱን አሉታዊ ተፅዕኖ መቀነስ እንደሚገባቸው ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ቭላድሚር ፑቲን ከኤርዶኻን ጋር ካደረጉት የስልክ ውይይት በኋላ ሩሲያ ከዩክሬን ወደ ቱርክ የሚላከውን ወጪ የእህል ንግድ ጨምሮ ከቱርክ ጋር ያላትን የባህር ትራንዚት አገልግሎት እና የሸቀጦች ንግድ ልውውጥ በተሻለ መልኩ ለማሳለጥ መስማማቷን አር ቲ ኒውስ ዘግቧል፡፡

ቱርክ ባቀረበችው ሩሲያ እና ዩክሬንን የማደራደር ሃሳብ ግን እስካሁን ድረስ ከሩሲያ በኩል የተሰጠ ምላሽ የለም፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.