Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ የሚያሳስባት የስዊዲንና ፊንላንድ የኔቶ አባል መሆን ሳይሆን ሀገራቱ ኔቶ ወታደራዊ መሰረተ ልማቱን እንዲያስፋፋባቸው የሚፈቅዱ ከሆነ ነው -ፕሬዚዳንት ፑቲን

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ የሚያሳስባት የስዊዲንና ፊንላንድ የኔቶ አባል መሆን ሳይሆን ሀገራቱ ኔቶ ወታደራዊ መሰረተ ልማቱን እንዲያስፋፋባቸው የሚፈቅዱ ከሆነ ነው አሉ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን።
የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሞስኮ በተካሄደው የጋራ የፀጥታ ስምምነት ድርጅት መሪዎች ጉባኤ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፥ የፊላንድ እና የስዊድን የኔቶ አባል መሆን የሩሲያ ስጋት አይደለም ብለዋል፡፡
ሆኖም “ሀገራቱ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ወታደራዊ መሰረተ ልማቱን እንዲተክልባቸው የሚፈቅዱ ከሆነ ግን ያ ምላሽ እንድንሰጥ የሚያስገድደን ስጋት ይሆናል” ነው ያሉት።
ሩሲያ የምትሰጠው ወታደራዊ ምላሽም በስዊዲንና ፊንላንድ ኔቶ የሚያደርገው ወታደራዊ እንቅስቃሴ ይወስነዋልም ብለዋል ፕሬዚዳንቱ።
ፊንላንድ እና ስዊዲን ለዓመታት የነበራቸውን የገለልተኝነት አቋም በመተው የኔቶ አባል ለመሆን መወሰናቸውን አስታውቀዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.