Fana: At a Speed of Life!

ራፋኤል ናዳል ኖቫክ ጆኮቪችን በመርታት 13ኛ የፍሬንች ኦፕን ድሉን አሳካ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ራፋኤል ናዳል በፍሬንች ኦፕን የሜዳ ቴኒስ የፍጻሜ ውድድር ኖቫክ ጆኮቪችን በማሸነፍ ባለድል ሆኗል፡፡

ውጤቱን ተከትሎም በፍሬንች ኦፕን የሜዳ ቴኒስ ለ13ኛ ጊዜ ባለድል መሆን ችሏል፡፡

ይህን ተከትሎም የወንዶች ግራንድ ስላም 20 ጊዜ በማሸነፍ የሮጄር ፌዴሬርን ክብረ ወሰን ተጋርቷል።

ናዳል በትናንቱ ጨዋታ የዓለም ቁጥር አንዱን ጆኮቪችን 6-0፣ 6-2 እና 7-5 በሆነ ውጤት ነው ያሸነፈው።

የትናንቱ ሽንፈት ለኖቫክ ጆካቪች በፈረንጆቹ 2020 የመጀመሪያው ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.