Fana: At a Speed of Life!

ሬድፎክስ የተሰኘ የመረጃ ቋት ማዕከል ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የዲጂታል ኢኮኖሚውን የሚያጠናክር ሬድፎክስ የተሰኘ የመረጃ ቋት ማዕከል ይፋ ሆነ፡፡

ማዕከሉ ይፋ ሲሆን የገንዘብ ሚኒስቴር ዴኤታ ዶክተር እዮብ ተካልኝ ንግግር አድርገዋል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታው በንግግራቸው መረጃ አዲሱ ነዳጅ ሲሉ ነው የተናገሩት፡፡

የዲጂታል መሰረተ ልማቱ መጠናከር በጤና፣በትምህርት፣ በግብርና እና በሌሎች መስኮች ላይ አስተዋጽዖውን ያሳርፋል ብለዋል፡፡

ሬድፎክስ ለረጅም ዓመታት በቴሌኮም ዘርፍና በመረጃ ቴክኖሎጂ ልምድ ባካበቱ የኢትዮጵያ ዳያስፖራዎች የተቋቋመ ነው፡፡

ሚኒስትር ዲኤታው ዳያስፖራዎቸ በዘርፉ ላይ በመሰማራታቸው ያላቸውን አድናቆት መግለጻቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.