Fana: At a Speed of Life!

አምራች ኢንዱስትሪዎችን ማብዛትና ማስፋፋት ምርጫ የሌለው ጉዳይ ነው- አቶ ደስታ ሌዳሞ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አምራች ኢንዱስትሪዎችን ማብዛትና ማስፋፋት ምርጫ የሌለው ጉዳይ ነው ሲሉ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ገለጹ፡፡

 

ርዕሰ መስተዳድሩ እና የካቢኔ አባላት በሀዋሳና አከባቢው የሚገኙ ከፍተኛና መካከለኛ አምራች ኢንዲስትሪዎች ጎብኝተዋል።

 

የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች የታቦር ሴራሚክስ ፋብሪካን፣ አማ የምግብ ዘይት ማቀነባበሪያ ፋብሪካን እና የሀዋሳ ጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ፓርክን ጨምሮ ሌሎችንም አገልግሎት እየሰጡ ያሉና ግንባታቸው በመጠናቀቅ ላይ ያሉ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።

 

የመስክ ምልከታው የ”ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ አካል ሲሆን÷ ውጤታማ አምራች ኢንዱስትሪዎች ልምዶቻቸውን በማስፋት የማምረት አቅምን ከፍ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

በጉብኝቱ ወቅት አቶ ደስታ ሌዳሞ ÷ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በመቀነስ በሀገር ውስጥ የመተካት ስራ እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

 

በክልሉ አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን ለመሳብ ዝግጅት መጠናቀቁን ጠቅሰው÷ አንዳንድ ፕሮጀክቶችን ለመደገፍ እየተሰራ  መሆኑን ነው የጠቆሙት፡፡

 

ሌሎች የሀዋሳ ጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ፓርክን ጨምሮ ሄሪ የወረቀት ፋብሪካ፣ አማ የምግብ ዘይት ፋብሪካ ግንባታ፣ የአቮካዶ ዘይት ማቀነባበሪያ፣ የአይዲን ጨው ማምረቻ፣ እንዲሁም የብስኩት ፋብሪካ ተጎበኝተዋል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.