Fana: At a Speed of Life!

ሰሜን ኮሪያ ለጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት ላከች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ ምዕራፍ የጀመረችበትን አዲስ መንግስት መመስረቷን እንዲሁም ዶክተር ዐቢይ አህመድ በድጋሚ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው መመረጣቸውን ተከትሎ በርካታ ሀገራት የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት እያስተላለፉ ይገኛሉ፡፡

ከእነዚህ ሀገራት መካከል ሰሜን ኮሪያ አንዷ ሆናለች፡፡

የሰሜን ኮሪያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪም ቶክ ሁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በድጋሚ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመመረጥዎ እንኳን ደስ አለዎት ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም÷ በስልጣን ዘመንዎ ለሀገርዎ ልማት፣ ብልጽግና እና ሰላም እንዲመጣ በሚያደርጉት ጥረት ሁሉ ስኬትን እመኝሎታለሁ ካሉ በኋላ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የሁለትዮሽ ግንኙነት፣ ወዳጅነት እና በትብብር የመስራት ፍላጎት እናጠናክራለን ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሪ ሰን ግዎን በበኩላቸው÷ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንንም እንዲሁ በድጋሚ በመመረጥዎ የእንኳን ደስ አለዎት መልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አክለውም÷ “በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው መልካም ግንኙነት እና ትብብር በቀጣይ በተጠናከረ መልኩ እናስቀጥላለን” ካሉ በኋላ በስራዎት ሁሉ ስኬትን እመኛለሁ ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአዲስ ምዕራፍ ጅማሮ አዲስ መንግስት ካዋቀረች በኋላ ቻይና ፣ሩሲያ ፣ቱርክ ፣ቬትናም ፣ኳታር ፣ ደቡብ ኮሪያ እና በርካታ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች የመልካም ምኞት መልዕክት ማስተላለፋቸውን አስታውሶ የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.