Fana: At a Speed of Life!

ሰሜን ኮሪያ እና ደቡብ ኮሪያ የባላስቲክ ሚሳኤል ሙከራ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሜን ኮሪያ እና ደቡብ ኮሪያ በዛሬው ዕለት የባላስቲክ ሚሳኤል ሙካራ ማድረጋቸው ተሰምቷል፡፡
 
ሰሜን ኮሪያ ባሳለፍነው ሰኞ ዕለት አዲስ የረጅም ርቀት ተወንጫፊ ሚሳኤል ሙከራ ማድረጓ ይታወሳል፡፡
 
ይህን ተከትሎም ሁለቱ ኮሪያዎች በጉዳዩ ዙሪያ ከፍተኛ ውዝግብ ውስጥ መግባታቸው ነው የተገለጸው፡፡
 
ሰሜን ኮሪያ የረጅም ርቀት ተወንጫፊ ሚሳኤል ሙከራ ካደረገች ከሁለት ቀናት በኋላም ባላንጣዋ ደቡብ ኮሪያ በዛሬው ዕለት የባለስቲክ ሚሳኤል ሙከራ አድርጋለች፡፡
 
ደቡብ ኮሪያ ሙከራውን ካደረገች ከሰዓታት ቆይታ በኋላም ሰሜን ኮሪያ የሁለት ባላስቲክ ሚሳኤሎች ሙከራ ማድረጓን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
 
ይህ የሁለቱ ሀገራት የሚሳኤል ሙከራ እሽቅድድምም በኮሪያ ልሳነ ምድር የተፈጠረውን ውዝግብ ይበልጥ እንዳያባብሰው ተሰግቷል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.