Fana: At a Speed of Life!

ሰሞኑን በጁባ 15 የጁንታው ተላላኪዎች ወደ ሀገራችን አንሄድም በማለት ጁባ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ሁከት ለመፍጠር ሞክረዋል – ሜ/ጄ መሃመድ ተሰማ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት በአህጉር አቀፍና በአለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ግዳጅ አኩሪ ተግባር እየፈፀመ እንደሚገኝ የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜ/ጄ መሃመድ ተሰማ ገለፁ፡፡

ከሰሞኑ የ15ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ በጁባ የሚገኘውን ቆይታውን ላጠናቀቀው ሰላም አስከባሪ ሀይል በመቀየር ላይ እያለ ፣ 15 የሰራዊት አባላት የጁንታው ተላላኪዎች ወደ ሀገራችን አንሄድም በማለት ጁባ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ በመንከባለልና በመጮህ ሁከት ለመፍጠር ሞክረዋል ብለዋል ፡፡

በመሆኑም እነዚህ የጁንታው ቅጥረኞች ፣ የሰራዊታችንን እና የሀገራችንን መልካም ስምና ዝና ለማጠልሸት ፣ በዩኤን የተለያዩ ቦታዎች ተቀጥረው የሚሰሩ የሰራዊት አባላት UNHCR የተባለውን ግብረ ሰናይ ድርጅት የሚዲያ ሽፋን እንዲያገኝ በማመቻቸት ጉዳዩን አለም አቀፍ ማህበረሰብ እንዲሰማው ለማደረግ የተሞከረ እንደነበርና ፣ በዚህም UNHCR ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ያስተጋባው ዘገባ ያልተገባ መሆኑን በመግለፅ ይቅርታ ሊጠይቅ እንደሚገባ ሜ/ጄ መሀመድ ተሰማ ተናግረዋል፡፡

አሁን ላይ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊታችን የጁንታውን ርዝራዦች አድኖ ለመያዝ በከፍተኛ ሞራልና ወኔ እየሰራ ባለበት ፣ በግለሰቦች እንዲህ አይነት ድርጊት መፈፀሙ ሰራዊታችንን የማይወክልና የግለሰቦች ብቻ እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባዋል ብለዋል፡፡

እነኝህ የሰራዊት አባላት ሌሎችን የማይወክሉ እንደሆኑና ፣ አሳፋሪ ተግባር የፈፀሙ ስለመሆናቸው ገልፀዋል፡፡

ይህንን ተግባርም እንደ ትልቅ ነገር እያራገቡ የሚገኙ የሚዲያ አውታሮችና ተከፋይ አምደኞችም ድርጊቱን በተገቢው በመረዳት ሚዛናዊነትን በመጠቀም ሊዘግቡት ይገባል  ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.