Fana: At a Speed of Life!

ሰራዊቱ በአሁኑ ሰዓት ከሁመራ እስከ ሽራሮ ያለውን ቦታ በማጥቃት የተለያዩ ስፍራዎችን በቁጥጥር ስር እያዋለ ነው- ሜ/ጄ መሐመድ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁመራና አካባቢው ሙሉ ለሙሉ በመከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር መዋሉን የሀገር መከላከያ ሰራዊት የኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል መሐመድ ተሰማ አስታወቁ።

ሰራዊቱ በአሁኑ ሰዓት ከሁመራ እስከ ሽራሮ ያለውን ቦታ በማጥቃት የተለያዩ ስፍራዎችን በቁጥጥር ስር እያዋለ እንደሚገኝም አመልክተዋል።

ሰራዊቱ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች ለሚኖሩ ሰዎች ድጋፍ ማድረግ የሚፈልጉ የእርዳታ ድርጅቶች ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር ተነጋግረው ድጋፍ ማድረግ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።

የህወሃት ጁንታ በአልመዳ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ የኤርትራ መከላከያ ሰራዊትን መለዮ በማዘጋጀት ላደራጃቸው ታጣቂዎች በማልበስ ኤርትራ እንደወረረች በመግለጽ ህዝብን እያደናገረ እንደሆነም  መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በዚህ የተቀናበረ ድራማ ህዝቡ ሳይታለል ለመከላከያ ሰራዊቱ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.