Fana: At a Speed of Life!

ሰው ሰራሽ የደህንነት መሳሪያዎች ከህክምና ባለሙያዎች በተሻለ መልኩ የጡት ካንሰርን እንደሚለዩ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 23፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አል የተባለ ሰው ሰራሽ መሳሪያ የጡት ካንሰር መመርመሪያ መሳሪያን በማንበብ ረገድ ከሐኪሞች በተሻለ ትክክለኛ መሆኑን አንድ ጥናት አመለከተ።

ሰው ሰራሹ መሳሪያ የጡት ካንሰር መመርመሪያ መሳሪያን በማንበብ ረገድ ሁለት ሐኪሞች በጋራ ከሚሰሩት በተሻለ መልኩ ትክክለኛ መሆኑን ባለሙያዎቹ አረጋግጠናል ብለዋል።

ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጣው ቡድን አል የተባለው ሰው ሰራሽ መሳሪያን ይዘው በ29 ሺህ ሴቶች ላይ ሙከራ ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

በዚህም መሳሪያው የጡት ካንሰርን በመለየት ረገድ የስድስት ራዲዮሎጂ ባለሙያዎችን ያክል ውጤታማ መሆኑንም ገልጸዋል።

ይህም ሁለት የዘርፉ ሐኪሞች (ዶክተሮች) ከሚሰሩት ስራ ጋር እኩል ውጤት ያለው ስለመሆኑም በጥናት ውጤታችን አረጋግጠናል ነው ያሉት።

ከዚህ ባለፈም መሳሪያው እንደ ሐኪሞቹና ራዲዮሎጂስቶቹ የግለሰቧን የቀደመ የጤና ሁኔታ የሚገልጽ መረጃ ሳይኖረው የጡት ካንሰሩን መለየት መቻሉም የተሻለ ስለመሆኑ ማሳያ ነው ብለዋል።

ባለው አሰራር ሁለት የራዲዮሎጂ ባለሙያዎች ችግሩን ለመለየት የጡት ካንሰር መለያ መሳሪያውን የሚያነቡ ሲሆን፥ ባልተስማሙባቸው ጉዳዮች ላይ ሦስተኛ ሐኪም ተጨምሮ ምስሎቹን እንዲገመግም ይደረጋል።

አዲሱ መሳሪያ ራሱን ችሎ ከማንበቡም በላይ ችግሩን ለይቶ በመረዳት በኩል ውጤታማ ስለመሆኑ በባለሙያዎቹ ተመስክሮለታል።

መሳሪያው የጡት ካንሰር ምርመራ ውጤት ላይ ከባለሙያዎቹ የተሻለ ውጤት ማስመዝገቡም ተገልጿል፤ በዚህም ለታካሚዋ የጡት ካንሰር አለብሽ በሚል በባለሙያ የሚነገራትን ሃሰተኛ የምርመራ ውጤት በ1 ነጥብ 2 በመቶ ቀንሷል።

ከዚህ ባለፈም በምርመራ ወቅት የጡት ካንሰር የለም በሚል የሚነገር የተሳሳተ ውጤት ደግሞ ከባለሙያ አንጻር መሳሪያው በ2 ነጥብ 7 በመቶ መቀነሱን ባለሙያዎቹ ገልጸዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.