Fana: At a Speed of Life!

ሱዛን ራይስን ጨምሮ የባራክ ኦባማ ዘመን ባለስልጣናት ሚሊየን ዶላሮችን ይዘው ወደ ነጬ ቤተ መንግስት ተመልሰዋል

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ባራክ ሁሴን ኦባማ ዘመን በሃላፊነት ላይ የነበሩ ግለሰቦች ጆ ባይደን ወደ ስልጣን ሲመጡ ሚሊየን ዶላሮችን በመያዝ ወደ ነጩ ቤተ መንግስት መግባታቸው ተገለፀ።

ኤቢሲ ይዞት በወጣው ሪፖርት በኦባማ የስልጣን ዘመን በተለያዩ የስራ ሃላፊነት የነበሩት እነዚህ ግለሰቦች ኪሳቸው በሚሊየን ዶላሮች ሞልቶ እና የግዙፍ ኩባንያዎችን ዓላማ አንግበው ተመልሰዋል ብሏል።

የኋይት ሀውስ ሃላፊ ሮን ክሊየን ፣ የሀገር ውስጥ ፖሊሲ ምክር ቤት ዳይሬክተር ሱዛን ራይስ፣ የብሄራዊ ኢኮኖሚክ ምክር ቤት ዳይሬክተር ብሪየን ዴሴ እና የኮሮና ቫይረስ ምላሸ አስተባባሪ ዚየንት ባለፉት ዓመታት ሀብታቸው በእጥፍ ጨምሮ ወደ ነጩ ቤተመንግስት እንደተመለሱ ሪፖርቱ አመላክቷል።

ሱዛን ራይስ በባራክ ሁሴን ኦባማ ዘመን ወደ ኋይት ሀውስ ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ አስገራሚ በሆነ መንገድ ሀብታቸው በእጅጉ መጨመሩን ኤቢሲ አገኘሁት ያለው ሪፖርት ያመላክታል።

በዚህም ከ36 እስከ 149 ሚሊየን ዶላር የሚገመቱ የተለያዩ ሀብቶች ማከማቸታቸውን ከሪፖርቱ ማረጋገጡን ነው መረጃው ያመለከተው።

ሱዛን ራይስ አሁን ጆንሰን ጆንሰን ፣ አፕል እና ማይክሮሶፍትን በመሰሉ ኩባንያዎች ከ250 ሺህ እስከ 5 ሚሊየን ዶላር የሚደርስ ሼር እንዳላቸው ተነግሯል።

በተመሳሳይ የኋይት ሀውስ ሃላፊና የረጅም ጊዜ የጆ ባይደን አማካሪ ሮን ክለየን ሀብት በሶስት እጥፍ መጨመሩ ተጠቁሟል።

የኮሮና ቫይረስ ምላሸ አስተባባሪ ዚየንትም በተለያዩ ዘርፎች ከ89 ሚሊየን ዶላር እስከ 442 ሚሊየን ዶላር የሚገመት ሀብት እንዳካበቱ ዘገባው አመልክቷል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.