Fana: At a Speed of Life!

ሱዳን በዳርፉር ያለውን የሰላም ማስከበር ሀይል ደህንነቱና ስርዓቱ ተጠብቆ እንዲወጣ እንድታደርግ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 23፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሱዳን በዳርፉር ያለውን የሰላም ማስከበር ሀይል ደህንነቱና ስርዓቱ ተጠብቆ እንዲወጣ እንድታደርግ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና የአፍሪካ ህብረት አሳሰቡ።
የተባበሩት መንግስታትና የአፍሪካ ህብረት በጥምረት በሱዳን ዳርፉር ያሰማሩት ሰላም አስከባሪ ኃይል ተልዕኮ መጠናቀቁ የሚታወስ ነው፡፡
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሀመት እና የተመድ ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በጋራ ባወጡት መግለጫ የሰላም አስከባሪ ኃይሉ (ዩናሚድ) በቀጣዮቹ ስድስት ወራት ደህንነቱ እና ስርዓቱ በተጠበቀ ሁኔታ እንዲወጣ ሱዳን ሀላፊነቷን እንድትወጣ አሳስበዋል።
ሙሳ ፋኪ መሀመት እና አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በአካባቢው የተገኘውን ሰላም ለማስቀጠል እና ሰላማዊ ዜጎችን ለመጠበቅ የተዘጋጀውን ብሄራዊ የተግባር አቅድ ለማስፈፀም አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን እንደገለፁ ፒፕልስ ዴይሊ ዘግቧል።
የሰላም አስከባሪ ኃይሉ (ዩናሚድ) ወታደሮች እና የፖሊስ ክፍል ከዛሬ ጀምሮ ዳርፉርን ለቆ ለመውጣት የሚያስችሉ ስራዎች ላይ እንደሚያተኩር ነው የተነገረው።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.