Fana: At a Speed of Life!

ሱዳን በዳርፉር 40 ሰዎች መገደላቸውን ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሱዳን በምዕራብ ዳርፉር ግዛት 40 ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸውን ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀች፡፡
በግዛቲቱ በተቀሰቀሰ የጎሳ ግጭት በጥቂቱ 40 ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል፡፡
በግዛቲቱ አል ጀኒና ከተማ ውስጥ በዓረብ እና መሳሊጥ ጎሳ ማህበረሰብ መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት ቢያንስ 40 ሰዎች መሞታቸውን እና ከ 50 በላይ መቁሰላቸውን ገልጿል፡፡
ከዚህ ባለፈም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተፈናቅለዋልም ነው የተባለው፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞም ተመድ በአካባቢው የፀጥታው ሁኔታ እስከሚሻሻል ድረስ የሰብአዊ አገልግሎት እንዲሁም የሰብአዊ በረራዎች መሰረዛቸውን አስታውቋል።
ከተማዋ ን ለሰብዊ እርዳታ ተደራሽ ለማድረግ እንደ ዋና ማዕከል ሆና የምታገለግል መሆኑን የጠቆመው ድርጅቱ አሁን በፀጥታ መደፍረስ ምክንያት ከ700 ሺህ በላይ ሰዎች ተጎድተዋል ነው ያለው፡፡
ባለፈው ጥር ወር በተከሰተ ተመሳሳይ ግጭት ቢያንስ 129 ሰዎች ለህልፈት ሲዳረጉ፥ ከ108 ሺህ በላይ ሰዎች እንዲፈናቀሉ ምክንያት መሆኑ ይታወሳል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of standing, outdoors and tree
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.