Fana: At a Speed of Life!

ሱዳን በጁባ የተደረሰውን የሰላም ስምምነት አፀደቀች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሱዳን ሉአላዊ ምክር ቤት እና የሱዳን ካቢኔ በደቡብ ሱዳን ጁባ የተፈረመውን የሰላም ስምምነት አፀደቁ።

የሱዳን ሉአላዊ ምክር ቤት እና የሱዳን ካቢኔ ትናንት ምሽት ባደረጉት የጋራ ስብሰባ ነው በዳርፉር ከሚገኙ አማጽያን ጋር የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተቀብለው ያፀደቁት።

ሉአላዊ ምክር ቤቱ እና ካቢኔው በጋራ ስብሰባቸው ከ10 ቀናት በፊት በጁባ የተደረሰው የሰላም ስምምነት ያደነቁ ሲሆን፥ ሁለቱን አካላት በማደራደር የተሳተፉ ከሚኒስትሮች የተውጣጡ ባለሙያዎችን እና ሌሎችንም አካላት ጥረት አድንቀዋል።

በትናንትናው እለት የሱዳን ፓርላማን በመተካት የተካሄደው የሉአላዊ ምክር ቤት እና የካቢኔ ስብሰባው በአብዱል ፈታህ አልቡርሃን የተመራ መሆኑም ታውቋል።

ከጋራ ስብሰባው በኋላ ባወጣው መግለጫም፥ የሰላም ሥምምነቱ ላይ የተሳተፉት የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪርና አደራዳሪ ቡድኑ ለሰላም ስምምነቱ ስኬታማነት ላደረጉት ጥረት ምስጋና አቅርቧል።

የሱዳን ሉአላዊ ምክር ቤት እና የሱዳን ካቢኔ ለስምምነቱ አፈጻጸም ምቹ ሁኔታን መፍጠርና አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ለማሟላት ከስምምነት መድረሳቸውም ተነግሯል።

ምንጭ፦ sudantribune.com

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.