Fana: At a Speed of Life!

ሱዳን የምንዛሪ ዋጋ ማሻሻያ አደረገች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የሱዳን ማዕከላዊ ባንክ የምንዛሪ ዋጋ ማሻሻያ ማድረጉን አስታወቀ፡፡

ማሻሻያው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት እና ለጋሾች የሽግግር መንግስቱን ለመደገፍ ያስቀመጡትን መስፈርት የሚያሟላ ነው ተብሏል፡፡

ማዕከላዊ ባንኩ በበኩሉ ማሻሻያው የዕዳ እፎይታ ለማግኘት እና የጥቁር ገበያውንና ህጋዊውን ምንዛሪ ለማጣጣም ያለመ መሆኑን ነው ያስረዳው፡፡

በሸቀጦች እጥረት እና በከፍተኛ ግሽበት አማካኝነት ማሻሻያው ለወራት ዘግይቶ እንደነበር ነው የተነገረው፡፡

ከማዕከላዊ ባንኩ የሚወጡ ይፋዊ ያልሆኑ ምንጮች ከዚህ ቀደም አንድ የአሜሪካ ዶላር በ55 የሱዳን ፓውንድ ሲመነዘር የነበረ ሲሆን አሁን በማሻሻያው በ375 ፓውንድ ሊያሽቆለቁል እንደሚችል ጠቅሰዋል፡፡

የጥቁር ገበያው ደግሞ በአሁኑ ወቅት አንድ የአሜሪካ ዶላርን ከ350 እስከ 400 የሱዳን ፓውንድ እንደሚያገበያይ ነው የተሰማው፡፡

በሌላ በኩል ለቀድሞ ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር ከስልጣን መነሳት ምክንያት የሆነው የኑሮ ውድነት አሁንም መቀጠሉ ተነግሯል፡፡

ዓለም ላይ ከተከሰቱት ሁሉ የከፋ ነው የተባለው የሀገሪቱ የዋጋ ግሽበት ዓመታዊ የግሽበት ምጣኔው ከ300 ፐርሰንት በላይ ነው ተብሏል፡፡

 

ምንጭ፡-አልጀዚራ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.