Fana: At a Speed of Life!

ሱዳን ደቡብ አፍሪካን በማሸነፍ ለአፍሪካ ዋንጫ አለፈች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሱዳን ደቡብ አፍሪካን 2 ለ 0 በማሸነፍ በካሜሩን አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ማለፏን አረጋገጠች።

ሱዳን በሜዳዋ ባፋና ባፋናዎችን አስተናግዳ ከእረፍት በፊት በተቆጠሩ ሁለት ጎሎች ከ12 ዓመታት በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ አልፋለች፡፡

ደቡብ አፍሪካ  ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ አቻ መውጣት በቂዋ የነበረ ቢሆንም ጠንካራ በነበረው የሱዳን ብሄራዊ ቡድን ዓላማዋን ሳታሳካ ቀርታለች።

በፈረንጆቹ 1970 የአፍሪካ ዋንጫ ያነሳችው ሱዳን ከ1976 በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ ስታልፍ ይህ ለሶስተኛ ጊዜ ብቻ ነው።

የደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ ቡድን (ባፋና ባፋና) ለአፍሪካ ዋንጫ አለማለፉ በሀገሪቱ ዜጎች ቁጭት ፈጥሮ በማህበራዊ የትስስር ገፆች ላይ ብሄራዊ ቡድኑ እንዲበተን ጥያቄ እንዲያቀርቡ አድርጓቸዋል።

በዚህ ምድብ ጋና ሳኦ ቶሜና ፕሪንሲፔን 3 ለ 1 አሸንፋ አንደኛ ደረጃን በመያዝ ለአፍሪካ ዋንጫ ስታልፍ ሱዳን ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ነው ለውድድሩ ያለፈችው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.