Fana: At a Speed of Life!

ሲመንስ የሕክምና መሳሪያ አምራች ኩባንያ ለጤና ሚኒስቴር 10 የአልትራ ሳውንድ ማሽኖች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጀርመኑ ሲመንስ የሕክምና መሳሪያ አምራች ኩባንያ ለጤና ሚኒስቴር 10 አልትራ ሳውንድ ማሽኖችን ድጋፍ አድርጓል፡፡

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ በተካሄደው የርክክብ መርሐ ግብር ላይ በኢትዮጵያ የጀርመን  አምባሳደር ስቴፋን ኦውየር፣ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሳህረላ አብዱላሂ፣ የሲመንስ ኩባንያ የኤክስፖርት ሽያጭ ዳይሬክተር ዶ/ር ኡው ቦርክ  እና የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ፕሮቮስት ዶ/ር ገዛወንድማገኝ ተገኝተዋል፡፡

በድጋፍ የተገኙት የአልትራ ሳውንድ ማሽኖች÷ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ በልዩ ልዩ የሕክምና ክፍል ተሰራጭተው አገልግሎት በመስጠት ላይ  እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

የአልትራሳውንድ ማሽኖቹ በኮሌጁ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል፣ ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመመርመር እንደሚያግዙ ተመላክቷል፡፡

ከዚህ ባለፈም ማሽኖቹ  ኮሌጁ የሚሰጠውን የሕክምና አገልግሎት ጥራት ለማሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳላቸው  መገለጹን  ከሆስፒታሉ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.