Fana: At a Speed of Life!

ሳዑዲ ዓረቢያ እና ባህሬን የኮቪድ 19 ክትባት ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ሳዑዲ ዓረቢያ እና ባህሬን የኮቪድ 19 ክትባት መርሃ ግብሮችን ጀምረዋል።

ሳዑዲ ዓረቢያ መጠነ ሰፊ የኮቪድ 19 የክትባት መርሃ ግብር ጀምራለች ፡፡

በባህረ ሰላጤዋ ሃገር ባለፈው ሳምንት  ጥቅም ላይ እንዲውል የተፈቀደውን የኮሮና ክትባት ከወሰዱት መካከል የጤና ሚኒስትሩ ቶፊቅ ራብያ አንዱ ናቸው፡፡

ላለፉት ዘጠኝ ወራት በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር በጭንቀት ተከታትያለሁ  ዛሬ ግን ክትባት የሚወስዱትን ሰዎችን በደስታ እከታተላለሁ ብለዋል ሚኒስትሩ፡፡

ወረርሽኙ ከተከሰተ ጀምሮ ሳዑዲ ዓረቢያ ከ300 ሺህ 300 በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሲሆን 6 ሺህ 80 ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳረግዋል ተብሏል፡፡

በተመሳሳይ ባህሬን የኮቪድ 19 ክትባት ብሄራዊ መርሃ ግብር ጀምራለች።

የባህሬን ንጉስ ሀማድ ቢን ኢሳ አል ካሊፋን የባህሬን ህዝብ ለቫይረሱ ከፍተኛ ትኩረት በማድረግ ሁሉንም የጥንቃቄ እርምጃዎች እና መመሪያዎችን ያከብራል ሲሉ አወድሰዋል።

ባህሬን 89 ሺህ 600 የሚሆኑ ዜጎቿ በኮቪድ -19 የተያዙ ሲሆን 349 የሚሆኑት ደግሞ ህይወታቸው ማለፉ ተገልጿል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.