Fana: At a Speed of Life!

ሴቶች ወደ ማረጥ ሲቃረቡ የድብርት ስሜት ያጋጥማቸዋል ተባለ-ጥናት

አዲስ አበባ፣ጥር 19፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ሴቶች ወደ ማረጥ ሲቃረቡ የድብርት ስሜት እንደሚያጋጥማቸው አንድ ጥናት አመለከተ፡፡

ጥናቱ እንዳመለከተው 40 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች የወር አበባ ማቋረጥ ወይም ማረጥ ሲያጋጥማቸው የድብርት ስሜት ያጋጥማቸዋል።

ሴቶች ከማረጣቸው በፊት ባሉ ዓመታት የሚከሰት ጭንቀት ከፍተኛ አደጋ እንዳለው ሊረዱ ይገባል ሲሉ የጥናቱ መሪና በሚሺጋን ዩኒቨርሲቲ የስነ-አዕምሮ ክፍል ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት ግሬስ ራላን ገልጸዋል፡፡

ከእነዚህም መካከል ሀዘን ፣ብስጭት፣እንቅልፍ ማጣት፣ ፍላጎት ማጣት ፣ ተደጋጋሚ የስሜት መለዋወጦች እንዲሁም ራስን የማጥፋት ሀሳቦችና ማጥፋት ይገኙበታል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም መደበኛ ያልሆነ የደም መፍሰስ እና ሌሎች ምልክቶች አንዲት ሴት የወር አበባዋ ሊቆም ወይም ልታርጥ ስትል ልታያቸው የምትችላቸው ምልክቶች ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል፡፡

በማረጥ ዕድሜ ላይ ባሉ ጉዳዮች ላይ ሥልጠና አለመኖር ለችግሩ መባባስ ምክንያት እንደሆነም ተገልጿል፡፡

ሴቶቹ ከማረጣቸው በፊት በሚፈጠረው ጭንቅት ዙሪያ የጋኒኮሎጂ ባለሙያዎች ምርመራ የማድረግ ልምድ እንደሌላቸው በጥናቱ ተመላክቷል፡፡

ከሴት የመዋለጃ ስርዓት እና ጡት ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ ህመሞችን ከሚያክሙት የጋኒኮሎጂ ባለሙያዎች መካከል ግማሽ ያህሉ ከማረጥ አስቀድሞ የሚከሰቱን እነዚህን ስሜቶች ለማከም በችሎታቸው እንደማይተማሙ ተጠቁሟል፡፡

ጥናቱ እነዚህ ባለሙያዎች ጭንቀትን በማከም ላይ ስልጠና ሊያገኙ ይገባል ሲል መክሯል፡፡

በጥናቱ ምን ያህሉ የጋኒኮሎጂ ባለሙያዎች ሴቶች ማረጥ ላይ ከመድረሳቸው ዓመታት በፊት የሚከሰትባቸውን ጭንቅት ያክማሉ በማለት ጥናት አድርጓል፡፡

በዚህ 197 የጋኒኮሎጂ ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን በውጤቱም 65 ነጥብ 9 በመቶዎቹ በማረጥ ላይ በሚገኙ ሴቶች ጭንቅት ስሜት ላይ ክትትል እንደሚያደርጉ ተመላክቷል፡፡

በሌላ በኩል 34 ነጥብ 1 በመቶዎቹ ደግሞ በማረጥ ላይ የሚገኙ ሴቶች የጭንቅት ስሜት ላይ ምንም አይነት ክትትል አያደርጉም፡፡

ምንጭ፡-reuters

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.