Fana: At a Speed of Life!

ስንከባበር፣ሰላማችን ስንጠብቅ፣ ግድባችንን እንገነባለን  ወደ ልማታችን  ፊታችንን እናዞራለን-ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 5፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ስንከባበር፣ሰላማችን ስንጠብቅ፣ ግድባችንን እንገነባለን  ወደ ልማችን  ፊታችንን እናዞራለን ሲሉ የኢትዮጵያ እሥልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ዒድሪስ ገለጹ።

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ዒድሪስ   እንኳን 1ሺህ 442ኛው ዓመተ ሂጅራ የኢድ ዓል ፈጥር  አደረሳችሁ እንኳን አደረሰን ብለዋል።

ዛሬ የሚከናወኑ 13 አስፈላጊ ሀይማኖታዊ ተግባራት  አሉም ሲሉ ገልጸዋል።

ከ13ቱ ተፈላጊ ጉዳዮች አንዱ ደስታ ነው ስለሆነም በዚህ በደስታ ቀን  ሰው  ቤተሰቡን ጎረቤቱን እና በአካባቢው ያሉ ሰዎችን ማስደሰት አስፈላጊ ነው ብለዋል።

በዚህም ያለንን ለጎረቤቶች፣ ለችግረኞች፣ ለአቅመ ደካማ አዛውንቶች በማካፈልና የታመሙ ሰዎችን መጠየቅ ሀይማኖታዊ ተግባር ነው ሲሉም ገልጸዋል።

እኛ ስንከባበር እኛ ስንዋደድ አንድነታችንን ከመጠበቅ ባለፈ ጠላታችንን አሳፍረን ድል በማድረግ ልማታችንን እናፋጥናለንም ነው ያሉት።

ስንከባበር፣ሰላማችን ስንጠብቅ፣ ግድባችንን እንገነባለን  ወደ ልማችን  ፊታችንን እናዞራለን ብለዋል፡፡

በዓሉን በሰላም እንድናከብር ላደረገው የኢትዮጵያ መንግስት በተለይም ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምስጋና አቀርባለሁ ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው÷ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈው በቅዱሱ የረመዳን ጾም ወቅት የተከናወኑ መልካም ተግባራት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል ።

የአብሮነት እሴቶቻችን እና  የውስጥ አንድነታችን በማጠናከር ከሁሉም አቅጣጫ የሚደረግብንን ጫና መከላከል አለብንም ነው ያሉት፡፡

በብሔርና በሐይማኖት ሊነጣጥሉን ሚፈሉጉ ሀይሎች ማወቅ ያለባቸው ፣ኢትዮጵያ ትንሽ ሲገፏት የምትወድቅ የእንቧይ ካብ አለመሆኗን ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያውያን ማንም ለመበደል ፍላጎት የሌላቸው እና በደልንም እሺ ብለው የማይቀበሉ ህዝቦች ናቸውም ነው ያሉት፡፡

ከድህነት ለመውጣት በምናደርገው ሂደት ውስጥ ኢ ፍትሃዊነት ባለመቀበል የጀመርነውን ልማታ አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.