Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በጥሎ ማለፉ ሞሮኮ ከስፔን እንዲሁም ፖርቹጋል ከስዊዘርላንድ ዛሬ ይጫወታሉ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 27 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኳታሩ ዓለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ዛሬም ቀጥለው ይካሄዳሉ። በዛሬው የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ማምሻውን 12 ሰዓት ላይ በሚካሄድ ጨዋታ አፍሪካዊቷ ሞሮኮ ከስፔን ይገናኛሉ። በሌላ ጨዋታ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ፖርቹጋል ከስዊዘርላንድ ጋር የምታደርገው ጨዋታም ከወዲሁ ተጠባቂ ሆኗል። ትናንት በተካሄደ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ክሮሺያ ጃፓንን በመለያ ምት 3 ለ 1 እንዲሁም ብራዚል ደቡብ ኮሪያን 4 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን መቀላቀላቸው ይታወሳል፡፡
Read More...

ብራዚል ደቡብ ኮሪያን 4 ለ 1 በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቀለች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኳታር ዓለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ብራዚል እና ደቡብ ኮሪያ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን አካሂደዋል፡፡ በዚህም የአምስት ጊዜ የዓለም ዋንጫ ሻምፒዮኗ ብራዚል ደቡብ ኮሪያን 4 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅላለች፡፡ የብራዚልን የማሸነፊ ግቦች ቪኒሺየስ ጁኒየር፣ ኔይማር…

በጥሎ ማለፉ ጃፓን ከክሮሺያ እንዲሁም ብራዚል ከደቡብ ኮሪያ ይጫወታሉ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም ዋንጫው የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ዛሬም ቀጥለው ይካሄዳሉ። በዛሬው የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ሁለቱ የእስያ ተወካዮች ጃፓን እና ደቡብ ኮሪያ ከክሮሺያ እና ብራዚል ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። ማምሻውን 12 ሰአት በሚካሄድ ጨዋታ ጃፓን ከክሮሺያ ይገናኛሉ። በምድብ 5 ስፔንን አስከትላ ያለፈችው ጃፓን ከ2018ቱ የዓለም…

ፈረንሳይ ፖላንድን በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቀለች

አዲስ አበባ፣ህዳር 25፣2015 (ኤፍ ቢሲ) በኳታር ዓለም ዋንጫ ፈረንሳይ ፖላንድን 3 ለ 1 በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅላለች፡፡ በአልቱማም ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የፈረንሳይን የማሸነፊያ ጎሎች ኦሊቪዬር ጂሩ እና ኬሊያን ምባፔ አስቆጥረዋል፡፡ የፖላንድን ብቸኛ ጎል ሮቤርቶ ሌቫዶቭስኪ በተጨማሪ ሰዓት በፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥሯል፡፡ ኦሊቪዬ ጂሩ በዛሬው ጨዋታ…

በቫሌንሲያ ማራቶን አትሌት አማኖ በሪሶ እና ለተሰንበት ግደይ አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት አማኖ በሪሶ እና ለተሰንበት ግደይ በስፔን ቫሌንሲያ ማራቶን ድል ቀንቷቸዋል፡፡ በስፔኑ የዛሬው የቫሌንሲያ ማራቶን ኢትዮጵያዊቷ አትሌት አማኖ በሪሶ ርቀቱን በ 2 ሰዓት 14 ደቂቃ ከ58 ሰከንድ በመጨረስ አዲስ ክብረ ወሰን አስመዝግባ አሸንፋለች። አትሌት ለተሰንበት ግደይ ደግሞ 2 ሰዓት ከ16 ደቂቃ ከ48 ሰከንድ…

በዓለም ዋንጫ ሩብ ፍጻሜውን ለመቀላቀል አፍሪካዊቷ ሴኔጋል የምታደርገውን ጨምሮ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 25 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ዋንጫው የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ዛሬም ቀጥለው ይካሄዳሉ። በዚህም መሰረት አመሻሽ 12 ሰዓት ላይ ፈረንሳይ ከፖላንድ ሩብ ፍጻሜውን ለመቀላቀል ይጫወታሉ፡፡ እንዲሁም ምሽት አራት ሰዓት አፍሪካዊቷ ሴኔጋል ሩብ ፍጻሜውን ለመቀላቀል ከኢንግሊዝ ጋር ትጫወታለች፡፡ ትናንት በተደረገ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ኔዘርላንድስ…