Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ  በኢሲኤ  መሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሂዷል፡፡ የጉባኤው ዋና አላማ የተሻሻለውን የመተዳደሪያ ደንብ ለማጽደቅ እንደሆነ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጂራ ተናግረዋል፡፡ ጉባኤው የተሻሻለው የፌዴሬሽኑ የመተዳደሪያ ደንብ  በጉባኤው ተሳታፊዎች በአብላጫ ድምጽ ካጸደቀ በኋላ የምርጫ ማስፈጸሚያ ደንብ  ረቂቅ ቀርቦ አስተያየት ተሰጥቶበት በአብላጫ ድምጽ  መጽደቁ  ተጠቁሟል፡፡ የምርጫ አስፈጻሚ…
Read More...

ሊቨርፑል የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫን አነሳ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሊቨርፑል ቸልሲን በፍጽም ቅጣት ምት በማሸነፍ የኤፍ ኤካ ፕ ዋንጫን አንስቷል፡፡ በዛሬው ዕለት ሊቨርፑል እና ቸልሲ ባደረጉት የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ መደበኛ እና ተጨማሪ 30 ደቂቃውን ያለ ምንም ግብ አጠናቀዋል፡፡ አሸናፊውን ለመለየት በተሰጡ የመለያ ምቶችም ሊቨርፑል ቸልሲን 6 ለ 5 በሆነ…

በፕሪሚየር ሊጉ መከላከያ እና ፋሲል ከነማ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በ23ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መከላከያ ሲዳማ ቡናን 5 ለ 3 አሸንፏል፡፡ ዛሬ ረፋድ 4 ሰዓት በተካሄደው እና ስምንት ጎሎችን ባስተናገደው ጨዋታ መከላከያ ከባህርዳር ስታዲየም ወሳኝ ሶስት ነጥብ ይዞ መውጣት ችሏል፡፡ ለመከላከያ ተሾመ በላቸው ሁለት ጎሎችን ሲያስቆጥር፥ ቢኒያም…

አሰልጣኝ ፍሬው ሃይለገብርኤል የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሰልጣኝ ፍሬው ሃይለገብርኤል የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆነው ተሾመዋል፡፡ በዚህ መሰረትም ከቀናት በኋላ በዩጋንዳ አስተናጋጅንት ይደረጋል ተብሎ በሚጠበቀው የሴካፋ ሴቶች እግርኳስ ውድድር ላይ ሉሲዎቹ በአሰልጣኝ ፍሬው ሃይለገብርኤል የሚመሩ ይሆናል፡፡ አሰልጣኝ ፍሬው ከ20 ዓመት በታች የሴቶቹን ብሔራዊ…

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የግብፅ አቻውን በማላዊ ቢንጉ ስታዲየም ያስተናግዳል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከግብፅ አቻው ጋር የሚያደርገው ጨዋታ በማላዊ ቢንጉ ስታዲየም እንዲካሄድ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ወስኗል፡፡ ቀደም ሲል ለኢንተርናሽናል ጨዋታዎች የተመረጠው የባህርዳር ስታዲየም የካፍ ደረጃን ባለማሟላቱ ካፍ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምታደርገውን ጨዋታ በሌላ ሀገር ስታዲየም እንድታደርግ…

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፐሪሚየር ሊግ መሪው ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥብ ጣለ

አዲስ አበባ፣ግንቦት 4፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ በተካሄደ ጨዋታ መሪው ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥብ ጥሏል፡፡ ፈረሰኞቹ ረፋድ 4 ሰዓት በባህርዳር ስታዲየም ከወላይታ ዲቻ ጋር ባደረጉት ጨዋታ ያለምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥብ መጣሉን ተከትሎ የነጥብ ልዩነቱን ለማጥበብ እና ወደ ዋንጫ ፉክክር ለመመለስ የፋሲል ከነማ…

አትሌት ለተሰንበት ግደይ በ2022 የቫሌንሺያ ማራቶን ላይ ትሳተፋለች

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 3 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ለተሰንበት ግደይ በ2022 የቫሌንሺያ ማራቶን ላይ ትሳተፋለች፡፡ በ5 ሺህ እና በ10 ሺህ ሜትሮች እንዲሁም በግማሽ ማራቶን የዓለም ክብረወሰንን የያዘችው አትሌት ለተሰንበት በ2022 የቫሌንሺያ ማራቶን ላይ እንደምትሳተፍ የዓለም አትሌቲክስ አስታውቋል። አትሌቷ…