Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ ወደ ግላስጎው አቀና

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ19ኛው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚካፈለው የኢትዮያ ልዑክ ወደ ግላስጎው አቀና፡፡ 19ኛው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከፈረንጆቹ መጋቢት 1 እስከ 3 ቀን 2024 በግላስጎው እንደሚካሄድ ይታወቃል፡፡ ኢትዮጵያን ወክሎ በውድድሩ ለሚካፈለው የልዑካን ቡድንም ዛሬ ዕኩለ ቀን ላይ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሽኝት ተደርጎለታል፡፡ በሽኝት ሥነ-ሥርዓቱም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉን ጨምሮ ሌሎችም አመራሮች…
Read More...

የኤቨርተን ቅጣት ወደ 6 ነጥብ ዝቅ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሦስት ወራት በፊት 10 ነጥብ ተቀንሶበት የነበረው ኤቨርተን ቅጣቱ ወደ 6 ነጥብ ዝቅ ተደርጎለታል፡፡ ኢቨርተን ነጥቡ ከመቀነሱ በፊት በሊጉ 14ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ የነበረ ሲሆን ከቅጣቱ በኋላ ወደ 19ኛ ደረጃ እንደወረደና ይህም በቡድኑ ውስጥ ድንጋጤ መፍጠሩ አይዘነጋም፡፡ በወቅቱ በተላለፈው ውሳኔ ቅር ተሰኝቶ…

በዓለም የቤት ውስጥ ውድድር ኢትዮጵያ በ14 አትሌቶች ትወከላለች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በስኮትላንድ በሚካሄደው የዓለም የቤት ውስጥ ውድድር ኢትዮጵያ በሥድስት ወንድ እና በስምንት ሴት አትሌቶች ትወከላለች፡፡ በዚህም መሰረት በሴቶች 800 ሜትር አትሌት ሀብታም ዓለሙ፣ ጽጌ ዱጉማ ሲካፈሉ ወርቅነሽ መሰለ በተጠባባቂነት ተይዛለች። እንዲሁም በ1 ሺህ 500 ሜትር አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ፣ ድርቤ ወልተጂ እና…

በወጣት ሴት 6 ኪሎ ሜትር ሩጫ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና በወጣት ሴት 6 ኪሎ ሜትር ሩጫ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸንፈዋል፡፡ 6ኛው የአፍሪካ ሀገር አቋራጭ ውድድር በቱኒዚያ ሃማማት መካሄድ ጀምሯል፡፡ ዛሬ በተካሄደው የወጣት ሴት 6 ኪሎ ሜትር ሩጫ ውድድርም÷ ሮቤ ዳዲ 1ኛ፣ የኔነሽ ሽመክት 2ኛ እንዲሁም ትነበብ አስረስ 3ኛ ደረጃን…

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቸስተር ዩናይትድ በሜዳው ተሸነፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ26ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በሜዳው ፉልሃምን ያስተናገደው ማንቸስተር ዩናይትድ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ተሸነፈ። በሳምንቱ ሌሎች ጨዋታዎች አስቶንቪላ ኖቲንግሃም ፎረስትን 4 ለ 2፣ ክሪስታል ፓላስ በርንሌይን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል። ኤቨርተንና ብራይተን ሆቭ አልቢዮንን 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት…

የኦሎምፒክ ችቦ የማብራት ንቅናቄ በሰመራ ከተማ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ) የኦሎምፒክ ችቦ የማብራት ንቅናቄ በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ተካሄደ።   በመጪው ሀምሌ ወር የሚካሄደውን የፓሪስ ኦሎምፒክ ምክንያት በማድረግ ሀገራዊ የኦሎምፒክ ችቦ ማብራት ንቅናቄ መጀመሩ ይታወቃል።   መቀሌን መነሻ በማድረግ የተጀመረው ሀገራዊ ንቅናቄ በአፋር ክልል በሰመራ ከተማ በሲምፖዚየምና…

6ኛው የአፍሪካ ሀገር አቋራጭ ውድድር በመጪው እሑድ መካሄድ ይጀምራል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 6ኛው የአፍሪካ ሀገር አቋራጭ ውድድር በመጪው እሑድ በቱኒዚያ ሃማማት መካሄድ ይጀምራል፡፡ ውድድሩ ለአራት ዓመታት ተቋርጦ የቆየ ሲሆን÷ ለስድተኛ ጊዜ በቱኒዚያ ሃማማት ከተማ ከፈረንጆቹ የካቲት 25 ቀን ጀምሮ እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡ በሻምፒዮናው ኢትዮጵያ በ14 ሴት እና በ14 ወንድ በአጠቃላይ በ28 አትሌቶች…