Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች የሴካፋ ዋንጫ ማጣሪያ ውድድርን ታስተናግዳለች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በሴካፋ ስር ከሚደረጉ ውድድሮች አንዱ የሆነውን ከ17 አመት በታች የምስራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውድድርን ታስተናግዳለች፡፡ በምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ብሄራዊ ፌዴሬሽኖች የተዋቀረው ሴካፋ በስሩ የሚደረጉ 7 ወድድሮችን የሚያስተናግዱ ሀገራት ዝርዝር ይፋ አድርጓል። የሴካፋ ዋና ዳይሬክተር አውካ ጌቼዮ እንደተናገሩት፥ ባለፉት ወራት ውድድር ለማዘጋጀት ጥያቄ ያቀረቡ ሀገራትን ለመምረጥ በትናንትናው እለት ስብሰባ ተደርጎ ሃገራቱ ተለይተው ተመርጠዋል። በውሳኔው…
Read More...

ተጠባቂው የሸገር ደርቢ ኢትዮጵያ ቡና ከቅዱስ ጊዮርጊስ የሚያደርጉት ጨዋታ ዛሬ ይደረጋል

አዲሰ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ተጠባቂው የሸገር ደርቢ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ከቅዱስ ጊዮርጊስ ዛሬ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይከናወናል፡፡ የሁለቱ ቡድን አሰልጣኞች ስለጨዋታው ያላቸውን አስተያየት ለሶከር ኢትዮጵያ ሰጥተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ቡናው አሰልጣኝ ካሳየ አራጌ ፥ ዝግጅታችን ጥሩ ነው፤ ደርቢ ሲሆን ስሜቱ ከበድ…

አትሌት አልማዝ አያና ወደ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ተመለሰች

አዲሰ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የ10 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰን ባለቤቷ አትሌት አልማዝ አያና ወደ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ተመልሳለች፡፡   በብራዚሉ ሪዮ ኦሊምፒክ የ 10 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰን ባለቤት የሆነችው አትሌት አልማዝ አያና ከእግር ጉዳት እንዲሁም ከወሊድ መልስ እንደገና ወደ ውድድር ተመልሳለች።   አትሌት አልማዝ…

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ የማራቶን ውድድሮች ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በተካሄዱ የተለያዩ የማራቶን ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል። በ2022 ኮሪያ -ዴጉ ዓለም አቀፍ ማራቶን ኢትዮጵያዊው አትሌት ሽፈራው ታምሩ አሸንፏል። በፈረንሳይ፣ ፓሪስ ዓለም አቀፍ ማራቶን በወንዶቹ አትሌት ጫሉ ዴሶ ገልሜሳ 2 ሰዓት ከ5 ደቂቃ ከ7 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመግባት አሸናፊ ሲሆን…

51ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር በመከላከያ ስፖርት ክለብ አሸናፊነት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለስድስት ተከታታይ ቀናት በሀዋሳ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ሲካሄድ የቆየው 51ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር በመከላከያ ስፖርት ክለብ አጠቃላይ አሸናፊነት ተጠናቀቀ። ከመጋቢት 19 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የተካሄደው የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ፍፃሜውን ዛሬ አግኝቷል። በዚህ ዉድድር…

የዓለም ዋንጫ የምድብ ድልድል ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 23 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2022 የኳታር የዓለም ዋንጫ የምድብ ድልድል ዕጣ አወጣጥ ስነ ስርአት ዛሬ በዶሃ ተካሂዷል። በምድብ 1 አስተጋጇ ኳታር፣ ኔዘርላንድስ፣ ሴኔጋል እና ኢኳዶር፤ በምድብ 2 ደግሞ እንግሊዝ፣ አሜሪካ፣ ኢራን እና የዌልስ/ስኮትላንድ ወይም ዩክሬን አሸናፊ፤ በምድብ 3 አርጀንቲና፣ ሜክሲኮ፣ ፖላንድ እና ሳዑዲ አረቢያ፤…

ክላረንስ ሴዶርፍ ከአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ጋር አዲስ አበባ ይመጣል

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 23 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የኔዘርላንድስ አማካይ ክላረንስ ሴዶርፍ ከአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ጋር አዲስ አበባ ይመጣል። የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ሚያዚያ 2 ቀን ቅዳሜ በሸራተን አዲስ ከቀኑ 7 ሰአት ጀምሮ በሚካሄድ ስነ ስርአት በተመልካች ይጎበኛል። ሴዶርፍም ከዋንጫው ጋር ሚያዚያ 2 ቀን ቅዳሜ በሸራተን አዲስ የሚገኝ…