Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ኢትዮጵያ የመላ አፍሪካ የአትሌቲክስ ውድድርን ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀቀች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)ኢትዮጵያ የመላ አፍሪካ የአትሌቲክስ ውድድርን በ18 ሜዳሊያ ናይጄሪያን በመከተል በ2ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች፡፡ ላለፋት አምስት ቀናት በጋና አክራ ዩንቨርሲቲ ሲካሄድ የቆየው 13ኛው የመላ አፍሪካ የአትሌቲክስ ውድድር ተጠናቋል። በውድድሩ ኢትዮጵያ በ47 ወንድ፣ በ40 ሴት በድምሩ በ87 አትሌቶች የተወከለች ሲሆን 7 የወርቅ፣ 7 የብር እና 4 የነሐስ በድምሩ 18 ሜዳልያዎችን ማስመዝገብ ችላለች፡፡ በውድድሩ ላይ ከ50 የአፍሪካ ሀገሮች ከ640 በላይ…
Read More...

ኢትዮጵያ በ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች ሩጫ ውድድር የወርቅና የብር ሜዳሊያ አገኘች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋና እየተካሄደ ባለው 13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ በ1 ሺህ 500ሜትር ሴቶች ሩጫ ውድድር የወርቅና የብር ሜዳሊያ አገኘች። በርቀቱ ለኢትዮጵያ የወርቅና የብር ሜዳሊያ ያመጡት አትሌት ሂሩት መሸሻ እና አትሌት ሀዊ አበራ ናቸው። በውድድሩ አትሌት ሂሩት መሸሻ 4:05.71 በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ውድድሩን…

ኢትዮጵያ በ5 ሺህ ሜትር ወንዶች ሩጫ ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋና እየተካሄደ ባለው 13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ በ5 ሺህ ሜትር ወንዶች ሩጫ ውድድር በሀጎስ ገብረህይወት አማካኝነት የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች። አትሌት ሀጎስ ገብረህይወት 13:38.12 በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ውድድሩን በቀዳሚነት አሸንፏል።

ኢትዮጵያ በሴቶች የቦክስ ውድድር 2 የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋና እየተካሄደ ባለው 13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ በ52 እና በ66 ኪሎ ግራም ሴቶች የቦክስ ውድድር 2 የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች። ቤተልሔም ገዛኸኝ ለሀገሯ የወርቅ ሜዳሊያ ያመጣችው በፍጻሜ ውድድሩ የሞሮኮዋን ቼዳል ራባብ 4ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ነው። በተመሳሳይ ኢትዮጵያዊቷ ቦክሰኛ…

አትሌት ዘውዲቱ አደራው በሴቶች ግማሽ ማራቶን የብር ሜዳሊያ አስገኘች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች የሴቶች ግማሽ ማራቶን ውድድር አትሌት ዘውዲቱ አደራው 2ኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ አስገኝታለች፡፡ አሁን ላይ የወንዶቹ የ20 ኪሎ ሜትር ውድድር እየተካሄደ ሲሆን÷ አትሌት ተሰማ መኮነን፣ማስረሻ ብሪ እና ሃፍታሙ አባዲ ኢትዮጵያን ወክለዋል፡፡

ኢትዮጵያ በሴቶች 10 ሺህ ሜትር ሩጫ ውድድር ብርና ነሐስ አስመዘገበች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ13ኛው የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሴቶች 10 ሺህ ሜትር ሩጫ ውድድር ብርና ነሐስ አስመዝግበዋል፡፡ በውድድሩ ውዴ ከፋለ ሁለተኛ የወጣች ሲሆን ፥ ተካን አማረ ሦስተኛ በመውጣት የብርና የነሐስ ሜዳሊያ ለሀገራቸው አስገኝተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በወንዶች የምርኩዝ ዝላይ የነሐስ ሜዳሊያ አገኘች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ13ኛው የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ በወንዶች የምርኩዝ ዝላይ የነሐስ ሜዳሊያ ማግኘቷን አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ገለጸ፡፡ ፌዴሬሽኑ እንዳለው ፥ የነሐስ ሜዳሊያውን ያገኘው አትሌት አበራ ለማ ሲሆን ፥ አራት ሜትር በመዝለል የነሐስ ሜዳልያውን እንዳጠለቀ ተገልጿል፡፡