Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

አቤል ያለው የግብጹን ዜድ ኤፍ ሲ ተቀላቀለ

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቅዱስ ጊዮርጊሱ አጥቂ አቤል ያለው የግብጹን ዜድ ኤፍ ሲ መቀላቀሉን ክለቡ አስታውቋል፡፡ ከታችኛው ሊግ በማደግ የግብጽ ፕሪሚየር ሊግን እየመራ የሚገኘው ዜድ ኤፍ ሲ  የቅዱስ ጊዮርጊሱን የፊት መስመር አጥቂ ለማስፈርም እንቅስቃሴ ሲያደርግ መቆቱ የሚታወስ ነው፡፡ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ቀሪ የአንድ ዓመት ኮንትራት የነበረው ተጫዋቹ ሊጠናቀቅ በተቃረበው የግብጽ የዝውውር መስኮት በይፋ ዜድ አፍ ሲን ተቀላቅሏል፡፡ በዚህም ከሳላሃዲን ሰዒድ ፣ ሽመልስ በቀለ ፣ ዑመድ ኡኩሪ እና ጋቶች ፓኖም…
Read More...

ማሊ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቀለች

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ዋንጫ ማሊ ቡርኪና ፋሶን 2ለ1 በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅላለች፡፡ ውጤቱን ተከትሎም ማሊ ሩብ ፍጻሜውን መቀላቀል ችላለች፡፡ ሞሮኮ እና ደቡብ አፍሪካ ደግሞ ምሽት 5 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል፡፡

የሀዋሳ ሃይቅ የግማሽ ማራቶን ውድድር የካቲት 3 ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 12ኛው የሀዋሳ ሃይቅ የግማሽ ማራቶን ውድድር የካቲት 3 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚካሄድ ታላቁ ሩጫ አስታወቀ። ውድድሩ ከዚህ ቀደም ይታወቅበት የነበረውን ስያሜ በመቀየር "የሀዋሳ ሃይቅ ግማሽ ማራቶን" በሚል ይካሄዳል ነው የተባለው። በዘንድሮው ውድድር ከወትሮው በተለየ ከእንግሊዝ፣ ከአሜሪካ፣ ጆርጂያ፣…

ኬፕ ቨርዴ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቀለች

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ዋንጫ ኬፕ ቨርዴ ሞሪታኒያን በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅላለች፡፡ ምሽት 2 ሰዓት በተደረገው የአፍሪካ ዋንጫ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ ኬፕ ቨርዴ ሪያን ሜንዴዝ ባለቀ ደቂቃ ባስቆጠራት የፍጹም ቅጣት ምት 1 ለ 0 አሸንፋለቸ፡፡ ውጤቱን ተከትሎም ኬፕ ቨርዴ በታሪኳ ለ2ኛ ጊዜ ሩብ ፍጻሜውን መቀላቀል ችላለች፡፡

በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮጵያ ቡና ሲያሸንፍ ወላይታ ድቻና ሃድያ ሆሳዕና አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ተደርገዋል፡፡ ቀን 9 ሰዓት ላይ በተካሄደ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ወልቂጤ ከተማን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ የኢትዮጵያ ቡናን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ አንተነህ ተፈራ በ33ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡ በተመሳሳይ ምሽት 12 ሰዓት ላይ…

የ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ሀገር አቀፍ የችቦ ቅብብሎሽ በመቀሌ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፈረንጆቹ የ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ሀገር አቀፍ የችቦ ቅብብሎሽ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በመቀሌ ከተማ ተከሂዷል። በችቦ ቅብብሎሽ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብሩ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር አትሌት ደራርቱ ቱሉ እና ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል። መርሐ-ግብሩ በመጪው ሐምሌ ወር 2016 ዓ.ም ለሚካሄደው…

አንጎላ ናሚቢያን በማሸነፍ  ሩብ ፍጻሜው ተቀላቀለች

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ አንጎላ ናሚቢያን 3 ለ 0 በማሸነፍ ወደ ሩብ ፍጻሜው ገብታለች፡፡ ምሽት 2 ሰዓት ላይ በቡዋኬ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አዲልሰን ነቡላ፣ ጊልሰን ዳላ እና ኦገስቲኖ ሙቡሉ ለአንጎላ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል፡፡ በጨዋታው የአንጎላው ግብ ጠባቂ አዲልሰን ኔብሉ እና የናሚቢያው…