Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀቁ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ተደርገዋል፡፡ ቀን 9 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ መድን እና ሻሸመኔ ከተማ ያካሄዱት ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል፡፡ የኢትዮጵያ መድንን ብቸኛ ግብ ወገኔ ገዛኸኝ ሲያስቆጥር÷ የሻሸመኔ ከተማን ደግሞ አብዱልቃድር ናስር አስቆጥሯል፡፡ በተመሳሳይ ምሽት 12 ሰዓት ላይ መቻል እና ፋሲል ከነማን ያገናኘው ጨዋታ 0 ለ 0 በሆነ ውጤት ተጠናቅቋል፡፡
Read More...

ሞሮኮ በአሰልጣኝ ዋሊድ ረግራጊ የሁለት ጨዋታዎች ቅጣት ይግባኝ ጠየቀች

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሞሮኮ በአሰልጣኝ ዋሊድ ረግራጊ የሁለት ጨዋታዎች ቅጣት ውሳኔ ላይ ለካፍ የይግባኝ ደብዳቤ ማስገባቷን የሀገሪቱ እግር ኳስ ፌደሬሽን አስታውቋል፡፡ አሰልጣኝ ዋሊድ ረግራጊ  አቻ በተጠናቀቀው የሞሮኮ እና ኮንጎ ጨዋታ በኮንጎ ብሄራዊ ቡድን አምበል ቻንሴል ምቤምባ ላይ በፈፀሙት ያልተገባ ባህሪ በካፍ የሁለት ጨዋታዎች እገዳ ተጥሎበት…

ምሽቱን የተካሄዱ የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ 5 ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀቁ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮቲዲቯር አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ በተመሳሳይ ሰዓት ምሽት ላይ የተካሄዱ የምድብ አምስት ሁለት ጨዋታዎች ያለምንም ጎል በአቻ ውጤት ተጠናቅቀዋል፡፡ ናሚቢያ ከማሊ እንዲሁም ደቡብ አፍሪካ ከቱኒዚያ ያደረጉት ጨዋታ ያለምንም ጎል በአቻ ውጤት ተጠናቅቋል፡፡ ይህን ተከትሎም ማሊ በ5 ነጥብ…

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የፊታችን ማክሰኞ ይጀመራል

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 53ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የፊታችን ጥር 21ቀን እንደሚጀመር የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡ መርሐ ግብሩ ከጥር 21 እስከ ጥር 26 ቀን 2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ለተከታታይ 6 ቀናት ነው የሚካሄደው፡፡ ውድድሩ  ክልሎች፣ ከተማ አስተዳደሮች፣ ክለቦችና ተቋማት የውድድር እድል…

ጋና አሰልጣኝ ክሪስ ሁተንን አሰናበተች

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጋና በአፍሪካ ዋንጫ ከምድብ አለማለፏን ተከትሎ የብሄራዊ ቡድን አሰልጣኙን ክሪስ ሂውተንን አሰናብታለች፡፡ ጋና በ2023ቱ የአፍሪካ ዋንጫ የሻምፒዮናነት ግምት ከተሰጣቸው አራት ቡድኖች አንዷ ብትሆንም ሳትጠበቅ የምድብ ተሰናባች ሀገር ሆናለች፡፡ የበርካታ ከዋከብቶች ስብስብ የሆነችው የጋና ከሞዛምቢክ እና ግብፅ ጋር አቻ…

ሴኔጋል ጊኒን 2 ለ 0 ካሜሮን ደግሞ ጋምቢያን 3 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ ምሽት 2 ሰዓት ላይ በተደረጉ የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ 3 ጨዋታዎች ሴኔጋል ጊኒን 2 ለ 0 ካሜሮን ደግሞ ጋምቢያን 3ለ2 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል፡፡ ቀድማ ማለፏን ያረጋገጠችው ሴኔጋል በ61ኛው እና በ90ኛው ደቂቃዎች በተቆጠሩ ግቦች አሸናፊ ሆናለች፡፡ ካሜሮንም በ56ኛው፣ 87ኛው እና በ91ኛው ደቂቃዎች…

አትሌት ለሜቻ ግርማ በፈረንሳይ ሌቪን በሚካሄደው የ3 ሺህ ሜትር ውድድር ይሳተፋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም የ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ክብረ ወሰን ባለቤት ለሜቻ ግርማ በፈረንሳይ ሌቪን በሚካሄደው የ3 ሺህ ሜትር ውድድር እንደሚሳተፍ ተገለፀ፡፡ አትሌቱ ባለፈው የውድድር ዘመን በፈረንሳይ ሌቪን በ3 ሺህ ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር በ7 ደቂቃ 23 ሰከንድ 81 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ሪከርድ ማሻሻሉ የሚታወስ ነው፡፡…