Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ሊዊስ ሱዋሬዝ ኢንተር ሚያሚን ለመቀላቀል ተስማማ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኡራጓዊው አጥቂ ሉዊስ ሱዋሬዝ በጥር የዝውውር መስኮት የአሜሪካውን ክለብ ኢንተር ሚያሚን ለመቀላቀል መስማማቱ ተገለፀ፡፡ ሱዋሬዝ በአንድ ዓመት የኮንትራት ውል ወደ ሜጀር ሊግ ሶከር ለማምራት በቃል ደረጃ ሥምምነት ላይ መድረሱ የተገለፀ ሲሆን÷ ይፋዊ ፊርማው በቅርቡ ይገለፃል ተብሏል፡፡ ሥምምነቱን ተከትሎም ሱዋሬዝ ከቀድሞው የባርሴሎና የቡድን አጋሩ ሊዮኔል ሜሲ ጋር በድጋሚ ይገናኛል ተብሏል፡፡ ሱዋሬዝ የአውሮፓ ቆይታውን በስፔኑ ክለብ አትሌቲኮ ማድሪድ ካጠናቀቀ በኋላ ወደ ብራዚሉ ግሬሚዮ…
Read More...

የሩሲያ እግርኳስ ወደ ኤሲያ ኮንፌዴሬሽን መዛወር እንደማይፈልግ ባለስልጣናቱ አስታወቁ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ ብሄራዊ ቡድን እና ክለቦች ወደ ኤሲያ ኮንፌዴሬሽን እንዲዛወሩ የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ የሞስኮ እግርኳስ ባለስልጣናት ውድቅ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል፡፡ የሩሲያ ብሄራዊ ቡድን እና ክለቦች በሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ምክንያት በፊፋ እና ከአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ውድድሮች አንዳይሳተፉ ማዕቀብ ተጥሎባቸው መቆየቱ…

ኧርሊንግ ሃላንድ የቢቢሲ የአመቱ ምርጥ ስፖርተኛ ሽልማትን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማንቼስተር ሲቲው አጥቂ ኧርሊንግ ሃላንድ የቢቢሲ የአመቱ ምርጥ ስፖርት ፐርሰናሊቲ ሽልማትን አሸንፏል፡፡ ኖርዌያዊው አጥቂ ክለቡ ማንቼስተር ሲቲ የሶስትዮሽ ዋንጫ ባሳካበት የ2022-23 የውድድር ዓመት በፕሪሚየር ሊግ፣ ቻምፒየንስ ሊግ እና ኤፍ ኤ ካፕ ውድድሮች 52 ጎሎችን አስቆጥሯል። ወጣቱ አጥቂ በ38 ጨዋታዎች 36…

ለባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታ ማጠናቀቂያ ከ900 ሚሊየን ብር በላይ ተፈቀደ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታ የቀሪ ሥራዎች ማጠናቀቂያ ከ900 ሚሊየን ብር በላይ መፈቀዱን የክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ገልጿል። የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ምስክር ሰውነት ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ ÷የማጠናቀቂያ ስራ ስታዲየሙ ዓለም አቀፍ ጨዋታዎችን ወደ…

የዩሮፓ ሊግ የጥሎ ማለፍ ድልድል ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣስ 8 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዩሮፓ ሊግ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ድልድል ይፋ ሆኗል። በጥሎ ማለፉ የጣሊያኑ ሮማ ከሆላንዱ ፊይኖርድ እንዲሁም ሌላኛው የጣሊያን ክለብ ኤሲሚላን ከፈረንሳዩ ሬንስ ጋር ተገናኝተዋል። የፈረንሳዩ ሌንስ ከጀርመኑ ፍሬይቡርግ የስዊዘርላንዱ ያንግ ቦይስ ከስፖርቲንግ ሊዝበን እንዲሁም ቤኔፊካ ከቱሉዝ ይጫወታሉ። ብራጋ…

በጥሎ ማለፉ ናፖሊ ከባርሴሎና  እንዲሁም ላዚዮ ከባየርን ሙኒክ ተገናኝተዋል

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ድልድል ይፋ ሆኗል። በድልድሉ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በጠንካራ አቋሙ የዘለቀው አርሰናል ከፖርቹጋሉ ፖርቶ ጋር ተገናኝቷል። በአንጻራዊነት ጠንካራ በሚመስለው ድልድል የጣሊያኑ ናፖሊ ከስፔኑ ባርሴሎና  እንዲሁም ሌላኛው የጣሊያን ክለብ ላዚዮ ከጀርመኑ ሃያል ክለብ ባየርን ሙኒክ ጋር…

ፊፋ 32 ክለቦች የሚሳተፉበት የዓለም ክለቦች ዋንጫ ውድድር ማዘጋጀቱን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) 32 ቡድኖች የሚሳተፉበት የዓለም ክለቦች ዋንጫ ውድድር ማዘጋጀቱን ይፋ አድርጓል፡፡ በቻምፒዮንስ ሊጉ በተለያዩ ዙሮች ተሳትፎ ያደረጉ ክለቦችን የሚያካትተው ይህ ውድድር በፈረንጆቹ 2025 ከሰኔ 15 እስከ ሀምሌ 13 በአሜሪካ እንደሚደረግ ነው የተገለፀው፡፡ የፊፋው ፕሬዚዳንት ጂያኒ…