Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መቻል ሲያሸንፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥብ ጣለ

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው 10ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መቻል ሲያሸንፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ አቻ ተለያይቷል፡፡ 9፡00 ላይ ሐዋሳ ከተማን የገጠመው መቻል 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡ የመቻልን ጎሎችም ምንይሉ ወንድሙ እና ከንዓን ማርክነህ ሲያስቆጥሩ÷ የሐዋሳ ከተማን ብቸኛ ጎል አሊ ሱለይማን አስቆጥሯል፡፡ ውጤቱን ተከትሎም መቻል ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በእኩል 23 ነጥብ ፕሪሚየር ሊጉን መምራት ሲችል÷ ሐዋሳ ከተማ በነበረበት 12ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡…
Read More...

 ለአፍሪካ ዋንጫ የተለያዩ ሀገራት ብሄራዊ ቡድኖች አቢጃን እየገቡ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአይቮሪኮስት አስተናጋጅነት ለሚደረገው የ2023ቱ የአፍሪካ ዋንጫ የተለያዩ ሀገራት ብሄራዊ ቡድኖች ወደ አቢጃን እየገቡ ይገኛሉ፡፡ ትናንት ምሽት የካሜሮኑ የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮን  የሴኔጋል  ብሄራዊ ቡድን ኮትዲቯር የገባ ሲሆን÷ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል ከልዑካን ቡድኑ ጋር አቢጃን ገብተዋል፡፡ የካሜሮኑ የአፍሪካ…

የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀቁ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 10ኛ ሳምንት የውድድር መርሐ ግብር የመጀመሪያ ቀን ውሎ ሁለት ጨዋታዎች ተካሂደዋል፡፡ ቀን 9 ሰዓት ላይ ሻሸመኔ ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና ያካሄዱት ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል፡፡ የሻሸመኔ ከተማን ግብ አብዱልቃድር ናስር ሲያስቆጥር÷ኢትዮጵያ ቡናን አቻ ያደረገችዋን ግብ ደግሞ…

ፍራንዝ ቤከንባወር ከዚህ አለም በሞት ተለየ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)የቀድሞው የምዕራብ ጀርመን እና የባየርሙኒክ ኮከብ ፍራንዝ ቤከንባወር በ78 አመቱ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል። ቤከንባወር በ1974 ጀርመን የዓለም ዋንጫን ስታነሳ ብሄራዊ ቡድኑን በአምበልነት መምራት የቻለ ሲሆን ÷በ1990 ደግሞ የጀርመን ብሄራዊ ቡድንን በአሰልጣኝነት እየመራ የዓለም ዋንጫን ማንሳት ችሏል፡፡ ባለ…

በዱባይ እና ዥያሜን ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2024 የዱባይ እና ዥያሜን ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ አሸንፈዋል፡፡ በዱባይ በወንዶች የተካሄደውን ውድድር አትሌት አዲሱ ጎበና ሲያሸንፍ÷ ለሚ ዱሜቻ 2ኛ፣ ደጀኔ መገርሳ 3ኛ እንዲሁም አብዲ ፉፋ 4ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቀዋል፡፡ በዚሁ የውድድር መርሐ-ግብር÷ አትሌት አንተን አየሁ ዳኛቸው 6ኛ፣…

በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ወላይታ ድቻ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣስ 27 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ9ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ወላይታ ድቻ ድል ቀንቷቸዋል፡፡ ቀን 9 ሰዓት ላይ በተካሄደ ጨዋታ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሀምበሪቾ ዱራሜን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ መሪነቱን አጠናክሯል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የማሸነፊያ ግቦች ባሲሩ ኡመር እና በረከት ግዛው ናቸው…

በፕሪሚየር ሊጉ ፋሲል ከነማ እና ኢትዮጵያ ቡና ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣስ 26 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ9ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማ እና ኢትዮጵያ ቡና ድል ቀንቷቸዋል። ከቀትር በኋላ በተካሄደ ጨዋታ ፋሲል ከነማ ድሬዳዋ ከተማን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል። የፋሲል ከነማን የማሸነፊያ ጎሎች ጌታነህ ከበደ እና ናትናኤል ገብረጊዮርጊስ አስቆጥረዋል፡፡ ምሽት 12 ሰዓት ላይ በተካሄደ ጨዋታ…