Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አዳማ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው 19ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አዳማ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸነፈ። 10፡00 ላይ በተካሄደው ጨዋታ አዳማ ከተማ ሙሴ ኪሮስ በ6ኛው ደቂቃ እና ቢኒያም አይተን በ54ኛው ደቂቃ ባስቆጠሯቸው ጎሎች አሸንፎ ወጥቷል። ቅዱስ ጊዮርጊስን ከሽንፈት ያላዳነችውን ጎል ታምራት እያሱ በ77ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል።
Read More...

አማኑኤል ገብረሚካኤል በጉዳት ላልተወሰነ ጊዜ ከሜዳ እንደሚርቅ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እና የፋሲል ከነማው አጥቂ አማኑኤል ገብረሚካኤል ባጋጠመው ከባድ ጉዳት ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ ከሜዳ እንደሚርቅ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ገለጹ፡፡ በውድ የዝውውር ገንዘብ ፋሲል ከነማን የተቀላቀለው አማኑኤል÷ ክለቡ ትላንት ከኢትዮጵያ ቡና ጋር አቻ በተለያየበት ጨዋታ ከግብ ጠባቂው ጋር በመጋጨቱ ነው…

ከእግርኳስ ሜዳ ስለምለያይበት ጊዜ አስቤ አላውቅም – ሊዮኔል ሜሲ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አርጀንቲናዊው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ በአሁኑ ወቅት ለኢንተርሚያሚ እየተጫወተ ይገኛል። ከወራት በኋላ 37ኛ ዓመቱን የሚይዘው ሊዮኔል ሜሲ ከቢግ ታይም ፖድካስት ጋር ባደረገው ቃል ምልልስ፤ የእድሜው መግፋት በእግርኳስ ህይወቱ ላይ የሚያመጣው ጫና እንደሌለ ተናግሯል። በመሆኑም በእግር ኳስ ሜዳ ላይ ስለሚያስመዘግበው ስኬት…

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች አለልኝ አዘነ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እና የባህርዳር ከተማ እግር ኳስ ክለብ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች አለልኝ አዘነ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። የባህርዳር ከተማ እግር ኳስ ክለብ እንዳስታወቀው፤ አለልኝ በጉዳት ምክንያት ከቡድኑ ተለይቶ በትውልድ ስፍራው አርባ ምንጭ ለእረፍት የሄደ ሲሆን ትናንት ምሽት በድንገት ህይወቱ አልፏል።…

በአፍሪካ ጨዋታዎች የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ አዲስ አበባ ገባ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋና በተካሄደው በ13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ ገብቷል። ልዑኩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ አቀባበል አድርገውለታል።…

በተለያዩ ሀገራት በተካሄዱ የሩጫ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት በተለያዩ ሀገራት በተካሄዱ የሩጫ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸንፈዋል፡፡ በቻይና ሁዋን ከተማ በተካሄደ የሴቶች ማራቶን ውድድር አትሌት ማሬ ዲባባ ርቀቱን 2 ሰዓት 25 ደቂቃ ከ12 ሰከንድ በማጠናቀቅ ቀዳሚ ሆናለች፡፡ በተመሳሳይ በጣልያን ሚላኖ ከተማ በተካሄደ የሴቶች ግማሽ ማራቶን ውድድር…

ኢትዮጵያ ሌሴቶን 2 ለ 1 አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በሁለተኛው ዙር የወዳጅነት ጨዋታ ሌሴቶን 2 ለ 1 አሸንፋለች፡፡ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው የአቋም መፈተሻ (የወዳጅነት ጨዋታ) ሌሴቶ በመጀመሪያው አጋማሽ ሌህሎሆኖሎ ፎቶአኔ ባስቆጠራት ብቸኛ ጎል እየመራች ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል፡፡ ይሁን እንጂ በሁለተኛው አጋማሽ ቸርነት ጉግሳ እና ከነዓን…