Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ከጃፓን መንግስት የተበረከተላትን የኒሻን ሽልማት ተረከበች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ከጃፓን መንግስት የተበረከተላትን የወርቅ ጨረር ያለው የኒሻን ሽልማት ተረክባለች። ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ በስፖርት ዲፕሎማሲ ላበረከተችው አስተዋፅኦ ቀደም ሲል ከጃፓን መንግስት የክብር ኒሻን ሽልማት የተበረከተላት መሆኑ ይታወሳል፡፡ በጃፓን እና በኢትዮጵያ መካከል ካበረከተችው የስፖርት ዲፕሎማሲ በተጨማሪ ለአትሌቲክስ እድገት እና ለሀገር ሰላም ላበረከተችው አስተዋፅኦም ነው ሽልማቱ የተበረከተላት፡፡ በዚህም…
Read More...

ለ45ኛው የዓለም አገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ልዑክ የእውቅና መርሐግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰርቢያ ቤልግሬድ በተካሄደው 45ኛ የዓለም አገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተሳትፎ በድል ለተመለሰው የልዑካን ቡድን የእውቅናና የማበረታቻ መርሐ ግብር ተካሂዷል፡፡ በመርሐ ግብሩ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ÷የተገኘው ውጤት አበረታች መሆኑን በመግለፅ ለቀጣይ ውድድሮች ትኩረት…

በ45ኛው የዓለም ሀገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለተሳተፉ አትሌቶች አቀባበል ተደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰርቢያ ቤልግሬድ በተካሄደው 45ኛው የዓለም ሀገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለተሳተፉ አትሌቶች በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ደማቅ አቀባበል ተደረጎላቸዋል፡፡ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነትና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ለአትሌቲክስ ቡድኑ…

ኢትዮጵያ የቦክስ ስፖርት ውጤታማ እንዲሆን ከፕሮጀክት ጀምሮ ሊሰራበት ይገባል – የቦክስ ስፖርተኞች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የቦክስ ስፖርት ውጤታማ እንዲሆን ከፕሮጀክት ጀምሮ በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባ በ13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታ በቦክስ ስፖርት ወርቅ ያስገኙት ስፖርተኞች ተናገሩ፡፡ የቦክስ ባለወርቆቹ ቤተልሄም ገዛኸኝ እና ቤተል ወልዴ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ ÷ ከዓመታት ቆይታ በኋላ በሴቶች የቦክስ…

አርሴናል እና ማንቸስተር ሲቲ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ30ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር አርሴናል እና ማንቸስተር ሲቲ ያደረጉት ጨዋታ ያለ ምንም ግብ ተጠናቋል፡፡ ውጤቱን ተከትሎም አርሴናል በ65 ነጥብ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ 2ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ሲቲ ደግሞ በ64 ነጥብ 3ኛ ደረጃን ይዟል፡፡ ቀደም ሲል ብራይተንን 2 ለ 1 ያሸነፈው ሊቨርፑል በ67…

በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ድሬደዋ ከተማ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው 19ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ድሬደዋ ከተማ 1 ለ 1 አቻ ተለያይተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ብቸኛ ግብ ሲሞን ፒተር ሲያስቆጥር÷የድሬደዋ ከተማን ደግሞ ቻርልስ ሙሲጌ አስቆጥሯል፡፡

ሊቨርፑል የሊጉን መሪነት ተረከበ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ30ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሊቨርፑል ብራይተንን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ የሊቨርፑልን የማሸነፈያ ግቦች ሉዊስ ዲያዝ እና ሞሃመድ ሳላህ አስቆጥረዋል፡፡ ብራይተንን ከሽንፈት ያላደነችውን ብቸኛ ግብ ደግሞ ዳኒ ዌልቤክ አስቆጥሯል፡፡ ውጤቱን ተከትሎም ሊቨርፑል የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን…