Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ተጫዋች እጩዎች ይፋ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2015 ዓ.ም የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ተጨዋች እጩዎች ይፋ ሆነዋል። በዚህ መሰረትም ቢኒያም በላይ እና እስማኤል ኦሮ አጎሮ ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ፉዓድ ፈረጃ ፣ያሬድ ባየህና  አለልኝ አዘነ ከባህር ዳር ከተማ፣ ባሲሩ ኡመር ከኢትዮጵያ መድኀን እንዲሁም ጌታነህ ከበደ  ከወልቂጤ ከተማ በእጩነት ቀርበዋል፡፡ በምርጥ በረኛ እጩ ዝርዝር ደግሞ አቦበከር ኑራ ከኢትዮጵያ መድን፣ ፔፔ ሳይዶ ከሀድያ ሆሳዕና እንዲሁም ቢኒያም ገነቱ ከወላይታ ድቻ በእጩነት መቅረባቸውን የሊግ ኩባንያው መረጃ…
Read More...

በስቶኮልም በተካሄደው ዳይመንድ ሊግ ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዊዲን ስቶኮልም በተካሄደው ዳይመንድ ሊግ ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በተለያዩ ርቀቶች ድል ቀንቷቸዋል። የ2023 የዳይመንድ ሊግ 7ኛው ዙር ውድድር በስቶኮልም የተካሄደ ሲሆን በ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች ውድድር ኢትዮጵያዊን አትሌቶች ተከታተለው በመግባት አሸንፈዋል። በዚህ የ1 ሺህ 500 ሜትር የሴቶች ውድድር…

ቅዱስ ጊዮርጊስ የ2015 ዓ.ም ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቅዱስ ጊዮርጊስ አንድ ጨዋታ እየቀረው የ2015 ዓ.ም ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መሆኑን አረጋግጧል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስን ከሀድያ ሆሳዕና ያገናኘው የ29ኛ ሳምንት ጨዋታ÷ 9፡00 ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ ስታዲየም ተካሂዷል፡፡ በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሀድያ…

በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮጵያ ቡና እና ለገጣፎ ለገዳዲ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ29ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ኢትዮጵያ ቡና እና ለገጣፎ ለገዳዲ ድል ቀንቷቸዋል፡፡ ቀን 9 ሰዓት ላይ በተደረገ ጨዋታ ከሊጉ መውረዱን ያረጋገጠው ለገጣፎ ለገዳዲ ከጥሩ የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ ጋር ሲዳማ ቡናን 3 ለ 2 መርታት ችሏል። ካርሎስ ዳምጠው፣አማኑኤል አረቦ እና ሱለይማን ትራኦሬ የለገጣፎ ጎሎችን…

በሪሁ አረጋዊ በሉዛን ዳይመንድ ሊግ በ5 ሺህ ሜትር የአመቱን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ አሸነፈ

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊው አትሌት በሪሁ አረጋዊ በሉዛን ዳይመንድ ሊግ በወንዶች 5 ሺህ ሜትር ድል ቀንቶታል። አትሌት በሪሁ ርቀቱን 12:40:45 በሆነ ጊዜ አጠናቆ የአመቱን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ አሸንፏል። በርቀቱ የሪከርዱ ባለቤት የነበረው ጆሹዋ ቸፕቴጌ 2ኛ ወጥቷል። የሃገሩ ልጆች ሃጎስ ገ/ህይወት 3ኛ፣ ጥላሁን ኃይሌ 4ኛ፣…

ባሕር ዳር ከተማ በአፍሪካ መድረክ ተሳታፊ መሆኑን አረጋገጠ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ባሕር ዳር ከተማ ኢትዮጵያ መድን ነጥብ መጣሉን ተክትሎ በአፍሪካ መድረክ ተሳታፊ መሆኑን አረጋግጧል፡፡ ዛሬ በተከናወነው የ29ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ጨዋታ አዳማ ከተማ ኢትዮጵያ መድንን 3 ለ0 አሸንፏል፡፡ ደስታ ዮሐንስ በመጀመሪያው አጋማሽ እንዲሁም ቢንያም አይተን እና አብዱል ከሪም ሞሐመድ (በራሱ…

በፕሪሚየር ሊጉ ድሬዳዋ ከተማ ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ29ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ሁለት ጨዋታዎች ዛሬ ተደርገዋል፡፡ ድሬዳዋ ከተማ እና አርባ ምንጭ ከተማ በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ባደረጉት ጨዋታ ድሬዳዋ ከተማ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል። የድሬዳዋ ከተማን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ አጥቂው ቢኒያም ጌታቸው በ72ኛው ደቂቃ ላይ…