Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

አዲስ አበባ የብሉምበርግ ብስክሌት መሰረተ ልማት ኢንሽዬቲቭ ሽልማት አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባ ከተማ የብሉምበርግ ብስክሌት መሰረተ ልማት ኢንሽዬቲቭ አሸናፊ ከሆኑ አስር የዓለማችን ከተሞች አንዷ ሆናለች። ከአምስት አህጉራት 275 ተወዳድረው ነው 10 ከተሞች የውድድሩ አሽናፊ የሆኑት። የብሉምበርግ ኢኒሼቲቭ አሸናፊዎቹ ሃገራት ፤ ኢትዮጲያን ጨምሮ ብራዚል ፣ ህንድ ፣ጣሊያን ፣ አልባኒያ ፣ ኒውዝላንድ ፣ፖርቹጋል ፣ ኮሎምቢያ ፣ ኬንያ ፣ሞዛምቢክ መሆናቸው ታውቋል። አዲስ አበባ በአፍሪካ ትልቁን የሳይክል ጎዳና ለመገንባት የጀመርቻቸው ስራዎችና ወደፊት ይህን ስኬት ከፍ…
Read More...

የኢትዮጵያ ሜዳ ቴኒስ ስፖርተኞች ልዑካን ቡድን ሽኝት ተደረገለት

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ ሀገራት አስተናጋጅነት በሚዘጋጀው የሜዳ ቴኒስ ውድድር ላይ የሚሳተፉ የኢትዮጵያ ስፖርተኞት ልዑካን ቡድን ሽኝት ተደረገለት። በኮንጎ ኪኒሻሳ እና በሩዋንዳ አዘጋጅነት በሚደረጉት የሜዳ ቴኒስ ሻምፒዮና እና ዓለምአቀፍ ውድድሮች ላይ የሚሳተፉት የወንዶች እና የሴቶች የስፖርት ልዑካን ቡድን ሽኝት እና የእራት ግብዣ…

ማንቼስተር ሲቲ የእንግሊዝ ኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ማንቼስተር ሲቲ የከተማ ተቀናቃኙን ማንቼስተር ዩናይትድ በማሸነፍ የእንግሊዝ ኤፍ ኤፕ ካፕ ዋንጫን አሸንፏል። 11 ሰዓት ላይ በተካሄደው የማንቹሪያ ደርቢ የፍፃሜ ጨዋታ ማንቼስተር ሲቲ በጀርመናዊዉ አጥቂ ኤልካይ ጎንዶጋን ጎሎች 2 ለ 1 በማሸነፍ ዋንጫውን ከፍ አድርገዋል። ሦስትዮሽ የዋንጫ ጉዟቸውን የቀጠሉት ስፔናዊው…

ቅዱስ ጊዮርጊስ የፕሪሚየር ሊጉን መሪነት ያጠናከረበት ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 24 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ27ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ሁለተኛ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ለገጣፎ ለገዳዲን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቶጎዋዊው አጥቂ ኢስማኤል ኦሮ አጎሮ በ16ኛው እና የአማካይ ተጫዋቹ ሀይደር ሸረፋ በ58ኛው ደቂቃ ለፈረሰኞቹ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።…

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከጎፈሬ የትጥቅ አምራች ድርጅት ጋር ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከጎፈሬ የትጥቅ አምራች ድርጀት ጋር  አዲስ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡ በአዲሱ ውል መሰረት ሀገር በቀሉ የትጥቅ አምራች ተቋም ጎፈሬ ለቀጣይ አራት ወራት ለኢትዮጵያ ወንዶች እና ሴቶች እግር ኳስ ቡድኖች ለውድድር እና ለልምምድ የሚሆን የትጥቅ አቅርቦት ያደርጋል። ጎፈሬ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ…

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ለ3ኛ ጊዜ አሰልጣኙን አሰናበተ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ኤሌክትሪክ ለሦስተኛ ጊዜ አሰልጣኙን አሰናብቷል፡፡ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ2011 ከፕሪምየር ሊጉ ከወረደ በኋላ ነበር በያዝነው ዓመት ዳግም መመለስ የቻለው። ክለቡ ከታችኛው የሊግ ዕርከን ካሳደገው አሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተና ጋር ለ7 የሊግ ጨዋታዎች ከቆየ በኋላ በምትኩ ለረዳት አሰልጣኙ ገዛኸኝ ከተማ ኃላፊነት በመስጠት…

ወልቂጤ ከነማ እና ኢትዮጵያ ቡና ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 21 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ26ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ወልቂጤ ከነማ እና ኢትዮጵያ ቡና ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡ ቀን 9 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ መድንን ያስተናገደው ወልቂጤ ከነማ 2 ለ 0 ማሸነፍ ችሏል፡፡ የወልቂጤ የማሸነፊያ ጎሎችን በእለቱ ድንቅ ብቃቱን ያሳየው ጌታነህ ከበደ በፍፁም ቅጣት ምት እና በጨዋታ ማስቆጠር…