Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ሀምበሪቾ ዱራሜ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ማደጉን አረጋገጠ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀምበሪቾ ዱራሜ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ማደጉን አረጋገጠ። 2006 ዓ.ም የተመሰረተው ሀምበሪቾ ዱራሜ ከአራት ዓመታት በኋላ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግን ተቀላቅሎ ሲሳተፍ መቆየቱን ሶከር ኢትዮጵያ አስነብቧል። ያለፉትን ዓመታት በሊጉ ሲሳተፍ ቆይቶ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ማደጉን አረጋግጧል።
Read More...

አቶ ውብሸት ደሳለኝ የብሄራዊ ቡድኑ የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)አቶ ውብሸት ደሳለኝ የዋሊያዎቹ የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ በመሆን መሾማቸውን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡ ፌዴሬሽኑ በቀጣይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን በጊዜያዊነት እንዲመሩ ኢንስትራክተር ዳንኤል ገብረማርያም እና አሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛውን በዋና አሰልጣኝ እና ምክትል አልጣኝነት መሾሙ ይታወሳል፡፡ የግብ…

የሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥብ ጥሏል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤትኪንግ ኢትዮጵያን ፕሪሚየር ሊግ የደረጃ ሰንጠረዥ እየመራ የሚገኘው ቅዱስ ጊዮርጊስ በሀዋሳ ከተማ ነጥብ ጥሏል፡፡ ቀን 9 ሰዓት ላይ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተደረገው የ24ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከእረፍት መልስ በቸርነት ጉግሳ ጎል መምራት ቢችልም ተባረክ ሄፋሞ በፍፁም ቅጣት ምት ጎል አስቆጥሮ ሀዋሳን…

ከ25ኛ ሳምንት በኋላ ያሉ ጨዋታዎች የዲ ኤስ ቲቪ ቀጥታ ስርጭት ሽፋን አያገኙም – ሊግ ኩባንያው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ25ኛ ሳምንት በኋላ ያሉ ጨዋታዎች የዲ ኤስ ቲቪ ቀጥታ ስርጭት ሽፋን እንደማያገኙ የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ አክሲዮን ማህበር አስታወቀ፡፡ ማህበሩ በማህበራዊ ትስስር ገፁ እንዳስታወቀው ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 ውድድር በሐዋሳ ከተማ እየተካሄደ መሆኑን እና ውድድሩ በቀጥታ የሱፐር ስፖርት ሽፋን እያገኘ…

በፕሪሚየር ሊጉ ፋሲል ከነማ ለገጣፎ ለገዳዲን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማ ለገጣፎ ለገዳዲን አሸነፈ፡፡ በዛሬው እለት 9 ሰዓት ላይ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደ ጨዋታ ፋሲል ከነማ ለገጣፎ ለገዳዲን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ የፋሲል ከነማ የማሸነፊያ ግቦችን የአማካይ ተጫዋቹ ሱራፌል ዳኛቸው በ45ኛው እና በ94ኛው ደቂቃ ላይ…

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በዛሬው እለት መጀመሩን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ገለጸ፡፡ 52ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ሲጀመር በሴቶች ርዝመት ዝላይ፣ በወንዶች ከፍታ ዝላይ የፍጻሜ፣ እንዲሁም በ800 ሜትር ወንዶችና ሴቶች ማጣሪያ ውድድሮች ተካሄደዋል። የውድድሩ ዓላማ በፈረንጆቹ ከታህሳስ 19 እስከ…

ኢንስትራክተር ዳንኤል ገብረማርያም የዋልያዎቹ ጊዜያዊ አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢንስትራክተር ዳንኤል ገብረማርያም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ጊዜያዊ አሰልጣኝ ሆነው መሾማቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን ላለፉት ሁለት ዓመታት ሲመሩ የቆዩት አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በስምምነት ከብሄራዊ ቡድኑ ጋር መለያየታቸው የሚታወስ ነው፡፡ ቀጣዩን አሰልጣኝ ለመምረጥ የሥራ…