Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ክሪስታል ፓላስ አሰልጣኝ ፓትሪክ ቪዬራን አሰናበተ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 8 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዙ እግር ኳስ ክለብ ክሪስታል ፓላስ አሰልጣኝ ፓትሪክ ቪዬራን ማሰናበቱን አስታወቀ። ክለቡ ፈረንሳዊውን የቀድሞ የአርሰናል አማካይ ከውጤት ማጣት ጋር በተያያዘ ከአሰልጣኝነት እንዳሰናበተው ቢቢሲ አስነብቧል። የደቡብ ለንደኑ ክለብ ባለፉት 12 ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም። በፕሪሚየር ሊጉም ከ27 ጨዋታዎች 27 ነጥብ በመሰብሰብ 12ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
Read More...

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቀጣይ ጨዋታዎች በአዳማ ከተማ ይካሄዳሉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከ18ኛ ሳምንት ጀምሮ በአዳማ ከተማ እንደሚካሄድ ሊግ ካምፓኒው አስታውቋል፡፡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አህጉራዊ ውድድር ምክንያት የተቋረጠው የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እስከ 17ኛ ሳምንት ድረስ በድሬዳዋ ከተማ ሲካሄድ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡ በቀጣይ ውድድሩ የሚካሄድበትን ከተማ…

አቡበከር ናስር ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ስብስብ ውጪ ሆነ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አቡበከር ናስር በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጊኒን ከሚገጥመው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ስብስብ ውጪ ሆኗል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጊኒ ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ ጥሪ ከተደረገላቸው ተጫዋቾች አንዱ የነበረው አቡበከር ናስር ከጉዳቱ ሙሉ ለሙሉ ማገገም ባለመቻሉ ነው ከዋልያዎቹ ስብስብ ውጪ የሆነው፡፡ በምትኩም የኢትዮጵያ…

በፕሪሚየር ሊጉ የ17ኛ ሳምንት ቀሪ ጨዋታዎች ለሌላ ተስተካካይ መርሐ ግብር ተዘዋወሩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 በ17ኛ ሳምንት ሊካሄዱ የነበሩ ቀሪ ጨዋታዎች ለሌላ ተሰተካካይ መርሐ ግብር ተዘዋውረዋል። በፕሪሚየር ሊጉ 2015 በ17ኛ ሳምንት በድሬዳዋ ስታዲየም ቅዳሜ መጋቢት 2 ቀን 2015 ዓ.ም የመጀመሪያ ጨዋታ 10 ሰዓት ሃዋሳ ከተማን ከኢትዮጵያ ቡና ያገናኘ ሲሆን÷ ጨዋታው ያለምንም ግብ…

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዉበቱ አባተ ከጊኒ ጋር ለሚያደርጉት የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል፡፡ በዚህም ግብ ጠባቂ ፋሲል ገብረ ሚካኤል ከባህርዳር ከነማ ፣ ሰዒድ ሃብታሙ ከአዳማ ከነማ  እና አቡበከር ኑራ ከኢትዮጵያ መድን ተመርጠዋል፡፡ በተከላካይ ክፍል ረመዳን የሱፍ፣ ሱሌማን ሃሚድ፣…

በፕሪሚየር ሊጉ ባህርዳር ከተማ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 3 ለ 1 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ባህርዳር ከተማ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 3 ለ 1 አሸነፈ፡፡ በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው የ16ኛ ሳምንት መርሐ ግብር የጣና ሞገዶቹ ከመመራት ተነስተው በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች በተከታታይ ባስቆጠሯቸው ጎሎች ሶስት ነጥብ አስመዝግበዋል፡፡ ለባህር ዳር ከተማ ሀብታሙ ታደሰ ሁለት ጎሎችን…

ኔይማር ጁኒየር እስከ ውድድር ዓመቱ መጨረሻ ወደ ጨዋታ እንደማይመለስ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ብራዚላዊው ኮከብ ኔይማር ጁኒየር እስከታድድር ዓመቱ መጨረሻ ድረስ ወደ ጨዋታ እንደማይመለስ ተገልጿል፡፡ የ31 ዓመቱ የፊት መስመር አጥቂ ክለቡ ፒኤስጂ ሊልን 4 ለ 3 ባሸነፈበት ጨዋታ ባጋጠመው የቁርጭምጭሚት ጉዳት ምክንያት ነው እስከ ውድድር ዓመቱ መጨረሻ ከሜዳ የራቀው፡፡ ኔይማር በፒኤስጂ ቆይታው በቀኝ እግሩ ላይ…