Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

አትሌት ለተሰንበት ግደይ የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ሻምፒዮን ሆነች

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአለምሻምፒዮና የ10ሺህ ሜትር አሸናፊዋ አትሌት ለተሰንበት ግደይ የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ሻምፒዮናን አሸነፈች፡፡ ውድድሩ ዛሬ ከማለዳ ጀምሮ ለ40ኛ ጊዜ በሱሉልታ ሲካሄድ የአለም ቻምፒዮኖች፣ የኦሊምፒክ ኮከቦችና ሌሎች ጠንካራ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተሳትፈዋል፡፡ የጃንሜዳን የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር በማሸነፏ በዚህ አመት በአውስትራሊያ በሚካሄደው የአለም አገር አቋራጭ ቻምፒዮና ኢትዮጵያን ወክላ የምትፋለም ይሆናል። እንዲሁም አትሌት ጌጤ አለማየሁ 2ኛ፣ አትሌት መቅደስ…
Read More...

ክሪስቲያኖ ሮናልዶ የሳዑዲ አረቢያውን አል-ናስር ተቀላቀለ

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 22 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፖርቹጋላዊ አጥቂ ክርስቲያኖ ሮናልዶ የሳዑዲ አረቢያውን ክለብ አል ናስርን ተቀላቀለ። የ37 አመቱ ሮናልዶ ከእንግሊዙ ማንቼስተር ዩናይትድ ጋር ከተለያየየ በኋላ አል ናስርን ለመቀላቀል መስማማቱ የሚታወስ ነው። ፖርቹጋላዊው ኮከብ ስሙ ከተለያዩ ክለቦች ጋር ሲያያዝ ቢቆይም የመጨረሻ ማረፊያው የሳዑዲው ክለብ ሆኗል።…

ከመጭው ጥር ወር ጀምሮ የስኳር አቅርቦት እጥረት እንደሚቀረፍ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከመጭው ጥር ወር ጀምሮ የስኳር አቅርቦት እጥረት እንደሚቀረፍ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ስራ አቁመው የነበሩ የስኳር ፋብሪካዎች ምርት ማምረት መጀመራቸውን ተከትሎ ነው ከመጭው ጥር ወር ጀምሮ የስኳር አቅርቦት እጥረት ይቀረፋል የተባለው፡፡ በጸጥታ ችግር እና በመለዋወጫ እጥረት ምክንያት የስኳር…

ብራዚል በኳስ ንጉሡ ፔሌ ሕልፈት ምክንያት 3 የሐዘን ቀናት አወጀች

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኳስ ንጉሡ ፔሌ ሕልፈት ምክንያት ብራዚል ሦስት የሐዘን ቀናት አወጀች፡፡ የብራዚሉ ፕሬዚዳንት ጃዬር ቦልሶናሮ የ82 ዓመቱን የኳስ ንጉሥ ፔሌ ሕልፈት ተከትሎ ሦስት ተከታታይ የሐዘን ቀን አውጀዋል። ብራዚላውያን በምንጊዜም ኮከባቸው ሕልፈት የተሰማቸውን ሐዘን እየገለጹ ነው። ፔሌ ከሀገሩ ብራዚል ጋር ሶስት የዓለም…

የእግር ኳስ ከዋክብት በፔሌ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም እግር ኳስ ከዋክብት በብራዚላዊው የምንጊዜም ኮከብ ፔሌ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን እየገለፁ ነው፡፡ የቀድሞዎቹ የብራዚል ከዋክብት ሮናልዶ ሉዊስ ናዛሪዮ ዴሊማ እና ሮናልዲንሆ ጎቾ በእግር ኳሱ ኮከብ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል። እንግሊዛዊው ጋሪ ሊንከርን ጨምሮ የቀድሞ ከዋክብቶች በፔሌ ህልፈት…

40ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል ሀገር አቋራጭ ውድድር የፊታችን እሑድ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 40ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል ሀገር አቋራጭ ውድድር  የፊታችን እሑድ በሱሉልታ ከተማ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ገለጸ። የፌዴሬሽኑ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት አትሌት ገዛኸኝ አበራ÷ በመጪው እሑድ በሚካሄደው 40ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል ሀገር አቋራጭ ውድድር ከ1 ሺህ 29 በላይ አትሌቶች ይካፈላሉ ተብሎ…

በቻን የአፍሪካ ሀገራት ውድድር የተሻለ ውጤት ለማምጣት እንሰራለን – አሰልጣኝ ውበቱ አባተ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻን የአፍሪካ ሀገራት ውድድር የተሻለ ውጤት ለማምጣት እንሰራለን ሲሉ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ገለጹ። አሰልጣኝ ውበቱ በአልጀሪያ የሚካሄደውን 7ኛው የቻን የአፍሪካ ሀገራት ውድድር ላይ ለመሳተፍ ብሄራዊ ቡድኑ ያደረጋቸውን ዝግጅቶች አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም÷ የኢትዮጵያ …