Fana: At a Speed of Life!

ሶማሊያ የ12 ዓመት ታዳጊን በመድፈር ለህልፈት የዳረጉ 2 ሰዎችን በሞት ቀጣች

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 3 ፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ምስራቅ ሶማሊያ የ12 ዓመት ሴት ልጅን በመድፈር ለህልፈት የዳረጉ ሁለት ግለሰቦች በሞት ተቀጡ።

አይሻ ኢሊያስ አዴን በአውሮፓውያኑ የካቲት  2019 በጋልካዮ በሚገኝ መኖሪያ ቤቷ ነበር ከተደፈረች በኋላ ተገድላ የተገኘችው።

በታዳጊዋ ላይ የተፈጸመውን ኢሰብዓዊ ድርጊት ተክትሎም በሀገሪቱ  ዜጎች ዘንድ ከፈተኛ ቁጣ ተቀስቅሶ ነበር።

ከወንጀሉ ጋር በተያያዘም 10 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ ሲደርግባቸው ቆይተዋል።

ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው  ፍድርቤትም በወንጀሉ ከተጠረጠሩት ግለሰቦች ውስጥ ሶስቱን ጥፋተኛ በማለት የሞት ቅጣት እንዲቀጡ ወስኗል።

የቅጣት ውሳኔው የዲ .ኤን. ኤ  ምርመራ ማስረጃ ውጤትን  መሰረት በማድረግ  የተላላፈመሆኑ ተመላክቷል።

በዚህ መሰረትም ጥፋተኛ ከተባሉት  ውስጥ አብዲፋታ አብዱራህማን ዋርሳም እና አብዲሻኩር ሞሃመድ የተባሉት ግለሰቦች  ዛሬ ጠዋት በቦሳሶ ከተማ አደባባይ በጥይት ተመተው ተገድለዋል።

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሶማሊያ ውስጥ አስገድዶ መድፈርና ወሲባዊ ጥቃት በከፍተኛ ሁኔታ የሚስተዋል መሆኑ ይነገራል።

የቅጣት ውሳኔው በሀገሪቱ በስፋት በሴቶች ላይ  የሚደርሰውን መሰል ጥቃት ለማስቀረት የሚያስችል አስተማሪ እርምጃ መሆኑ ተመላክቷል።

ምንጭ፡-ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.