Fana: At a Speed of Life!

ሶስቱ የትግራይ ክልል የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች በ2014 የውድድር ዘመን በፕሪሚየር ሊጉ የመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ሶስቱ የትግራይ ክልል የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች በ2014 የውድድር ዘመን በፕሪሚየር ሊጉ የመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው አሳወቁ።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዛሬ ግንቦት 24ቀን 2013ዓ.ም ከ3ቱም የትግራይ ክልል የፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦች ጋር ስለ ቀጣይ የውድድር ዘመን ተሳትፏቸው በተመለከተ ውይይት አደረገ።
በውይይቱ ክለቦቹ በአሁን ወቅት ያሉበትን ነባራዊ ሁኔታ አስረድተው ወደ ውድድር ለመመለስ ፍላጎት ቢኖራቸውም ፋይናንስ ትልቅ ችግር እንደሚሆንባቸው ተናግረዋል።
ከውይይቱ ያገኟቸውን የሀሳብ ግብዓቶች በመውሰድ ወደ ክለቦቻቸው በመመለስ፣ ከደጋፊዎቻቸው ፣ ከክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ጋር በመነጋገር በአጭር ጊዜ ውስጥ የመጨረሻ ውሳኔያቸውን እንደሚያሳውቁ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንም ክለቦቹ ወደ ውድድር እንዲመለሱ ለማድረግ በሚችለው ሁሉ ለማገዝ ዝግጁ መሆኑን መግለፁን ከፌደሬሽኙ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በውይይቱ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራን ጨምሮ የመቐለ 70 እንደርታ፣ የወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሲቲ ፣ የትግራይ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ የትግራይ ክልል ስፖርት ኮሚሽን አመራሮች በአካል የተገኙ ሲሆን የስሁል ሽረ አመራሮች በአካል መገኘት ባለመቻላቸው በቴሌ ኮንፍረንስ ተሳትፈዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.