Fana: At a Speed of Life!

ሸማችና አምራችን በቀጥታ ማገናኘት የሚያስችል የግብይት ስርዓት ለመዘርጋት በልዩ ትኩረት ይሰራል-ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 25 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሸማችና አምራችን በቀጥታ ማገናኘት የሚያስችል የግብይት ስርዓት ለመዘርጋት በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለፁ ።
በአዲስ አበባ ከተማ በሶስት አካባቢዎች የተገነቡ ዘመናዊ እና ሁለገብ የአትክልት ፣ የፍራፍሬ እና የሰብል ምርቶች መገበያያ ማዕከላት ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል ።
ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እና ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የላፍቶ አትክልትና ፍሬፍሬ የገበያ ማዕከል ፣ ጀሞ ሁለገብ የገበያ ማዕከል እና ፉሪ ሁለገብ የሴቶች የገበያ ማዕከል በዛሬው እለት ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል ።
ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በገበያ ማዕከላቱ የምርቃት ስነስርዓት ላይ ÷ በከተማዋ ሸማችና አምራች በቀጥታ ማገናኘት የሚያስችል የግብይት ስርዓት ለመዘርጋት በልዩ ትኩረት ይሰራል ብለዋል ።
በሌሎች አካባቢዎችም መሰል የአትክልት ፣ የፍራፍሬ እና የሰብል እህል መገበያያ ማዕከላት ግንባታ እንደሚካሄድ ምክትል ከንቲባዋ ጠቁመዋል።
በዛሬው ዕለት ለአገልግሎት ክፍት በተደረጉ ማዕከላት የላፍቶ አትክልትና ፍራፍሬ 556፣የጀሞ ሁለገብ የገበያ ማዕከል 126 እና ፉሪ ሁለገብ የሴቶች የገበያ ማዕከል 298 በጠቅላላው 980 ሱቆችን ሲሆኑ ለበርካቶች ዜጎች የስራ እድል በመፍጠር ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸውን ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሰክሬተሪያት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.