Fana: At a Speed of Life!

ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ በጎንደር ከተማ ለአካል ጉዳተኞች 48 ዊልቼሮችን አበረከቱ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 5 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው በጎንደር ከተማ ለሚገኙ ለአካል ጉዳተኞች 48 ዊልቼሮች አበረከቱ።

በተመሳሳይ በከተማ ለሚገኙ አምስት አይነ ስውራን ተማሪዎች የብሬይል ኮምፒውተሮችን ቀዳማዊት እመቤቷ አበርክተዋል።

ቀዳማዊት እመቤቷ የደባርቅ ብርሃን እና ሳህላ ብርሃን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ካስመረቁ በኋላ በጎንደር ከተማ በተካሄደ ስነ ስርዓት ላይ ነው ለአካል ጉዳተኞቹ እና ለተማሪዎች ያበረከቱት።

በዚህ ወቅት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድርን አቶ አገኘሁ ተሻገር ጨምሮ ሌሎች የክልልና የከተማ የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል።

የጎንደር ከተማ ከንቲባ አቶ ሞላ ቀዳማዊቷና ፅህፈት ቤታቸው ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት ለመመለስ የትምህርት ቤት ግንባታ ከማከናወን ባሸገር እነዚህ ቁሳቁሶች ድጋፍ ማድረጋቸው የሚደነቅ ነው ብለዋል።

ድጋፉ የተበረከተላቸው ዜጎች በጎንደር ከተማ ሰራተኛ እና ማህበራዊ ፅህፈት ቤት የተለዩ መሆናቸው ተጠቁሟል።

በፍሬህይወት ሰፊው

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.