Fana: At a Speed of Life!

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ፥ የሥጋ ደዌ ተጠቂ የሆኑ የማህበረሰብ አባላትን ተጠቃሚ የሚያደርግ የቤት እድሳት አስጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የሚኖሩ የስጋ ደዌ ተጠቂ ማህበረሰብ አባላትን ተጠቃሚ የሚያደርግ የቤት እድሳት በዛሬው ዕለት አስጀምረዋል፡፡
የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ከክረምት በፊት ተጠናቀው የሚያልቁ የስድስት አባወራ ቤቶችን እንደሚያድስ በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ተገልጿል፡፡
የቤት እድሳቱ በማህበረሰቡ ዘንድ የተዘነጉትን የስጋ ደዌ ተጠቂ ማህበረሰብ አባላት ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
የቤት እድሳቱ ተጨማሪ ተጠቃሚዎችን በማካተት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ከቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.