Fana: At a Speed of Life!

ቀጠናዊ እና ሀገራዊ ሁኔታውን ያገናዘበ የፀጥታ ስራ በመስራት በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ተሰርቷል-አቶ ሞላ መልካሙ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጥምቀት በዓልን በሰላም ለማክበር ዝግጁቱን ማጠናቀቁን የጎንደር ከተማ አስታወቀ።
 
ዛሬ ከሰዓት መግለጫ የሰጡት የከተማዋ ከንቲባ አቶ ሞላ መልካሙ÷ ቀጠናዊ እና ሀገራዊ ሁኔታውን ያገናዘበ የፀጥታ ስራ በመስራት በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ስለመሰራቱ አውስተዋል።
ከፀጥታው እኩል ለኮሮና ቫይረስ ትኩረት በመስጠት 400ሺህ ማስክ እና 5000ሺህ ሳኒታይዘሮች ስለመዘጋጀታቸውም ተናግረዋል።
ባለፈው ዓመት የተፈጠረው የመቀመጫ መውደቅ አይነት ሁኔታ እንዳይፈጠር በእንጨት የነበረውን ወደ ብረት የመቀየር ስራም ተሰርቷል ብለዋል።
ከዚያም ባለፈ መጨናነቁን ለማስቀረት ጠበል ከጥምቀተ ባህሩ ተነስቶ በአራት አቅጫጫዎች እንዲፈፀም ዝግጅቱ ስለመጠናቀቁም ነው የገለጹት።
በጥምቀተ ባህሩ የሚገቡ ሰዎችን ቁጥር ለመቀነስ በማሰብም 4 የባህረ ጥምቀቱን ሁኔታ የሚያሳዩ እስክሪኖች ስለመገጠማቸው በመግለጫቸው አንስተዋል።
በክብረወሰን ኑሩ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.