Fana: At a Speed of Life!

ቀጣዩ ምርጫ ወደ ብሄራዊ መግባባት የምንሻገርበት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ የሚካሄድ እንደመሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሊጠቀሙበት ይገባል- ምሁራን

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 22፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ቀጣዩ ምርጫ ወደ ብሄራዊ መግባባት የምንሻገርበት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ የሚካሄድ እንደመሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሊጠቀሙበት ይገባል ሲሉ የሶዶ ዩኒቨርስቲ የማህበረሰብ ሳይንስ መምህር ንጋቱ አበበ ገልጸዋል ።

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ የነበራቸው የማህበረሰብ ሳይንስ ምሁሩ፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሀገሪቱ ያለችበትን ሁኔታ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የማህበረሰቡን ጥያቄ እና የልብ ትርታ መልስ የሚሆኑ የፖሊሲ አማራጮችን እንዲያዘጋጁ ይጠበቃልም ነው ያሉት።

በርግጥ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ አማራጭ ሀሳቦችን የማዘጋጀት ውስንነት እንደሚስተዋልባቸውም አንስተዋል ።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እጩ የህግ ዶክተር ረዲ ሲርበሮ ፓርቲዎች አማራጭ ሀሳቦች ላይ ከማተኮር ይልቅ የብሽሽቅ ፖለቲካ ላይ ጊዜያቸውን ያባክናሉ፤ ይህም ህዝብ የሚፈልጓቸውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ላይ አማራጭ ሀሳብ እንደማቅረብ የተሳትፎ ብቻ ሩጫን በምርጫው ያደርጋሉ ነው የሚሉት ።

የሌሎች ሀገራትን ተሞክሮ የሚያነሱት የህግ ምሁሩ የተደራጀ ግዙፍ ሀሳብን በምርጫ ወቅት በማንሳት ለመራጩ ህዝብ አማራጭ ሆነው ብቅ ይላሉ፤ መራጩም ለሀገሩ ይበጃል ያለውን ፓርቲ ለመምረጥ አይቸገርም ብለዋል።

በ6ተኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተለይ ከነባራዊው የሀገሪቱ ሁኔታ አንጻር ብሄራዊ መግባባትን ሊያጸኑ የሚችሉ እንዲሁም ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ወደ ተሻለ ምእራፍ ሊያሻግሩ የሚችሉ ሀሳቦችን ማዘጋጀት ይኖርባቸዋል ብለዋል አቶ ንጋቱ አበበ።

ወሳኝ በሆነው ቀጣዩ ምርጫ ተሳታፊ ከሆኑት ፓርቲዎችም ትልቁ የቤት ስራ ይህ ይሆናል ነው ያሉት ።

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ለአመታት ፓርቲዎቹ እንደመመላለሳቸው ‘‘ የህዝብ ፍላጎት ምንድን ነው? ’’ ከሚል ቅኝት የፖሊሲ ሀሳብ አዘጋጅት ተፎካካሪ መሆኑም ይችላሉ ብለዋል ።

በፓርቲዎች መካከል የፖሊሲ ክርክር ልምድ ሊዳብርና አማራጫችን ይሄ ነው ብለው ወደፊት በመውጣት ለህዝቡም የማሳወቅ ተግባርን ሊለማመዱት ይጠበቃል ።

የተደራጀ ሀሳብ የማዘጋጀት እና ለመራጩ የፖለቲካ ፤ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ችግሮቹ መውጫ መፍትሄን የማዘጋጀት ልምድ እንዲዳብር መክረዋል ።

ከወዲሁም በምርጫው ሂደት ወሳኝ በሆነው የቅድመ- ምርጫ የፖሊሲ ዝግጅት ላይ አማካሪ ምሁራንን ጭምር የሀሳብ ማጠናከሪያ በመጠየቅ ዝግጅት ማድረግ እንዳለባቸው አንስተዋል ።

በብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ግንቦት 28 ቀን 2013 ዓ.ም የድምጽ መስጫ ቀን ሆኖ መቅረቡ የሚታወስ ነው ።

በሀይለየሱስ መኮንን

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅ ታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.