Fana: At a Speed of Life!

ቃሪያን መመገብ  በልብ በሽታ እና በጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስ የመሞት አደጋን ይቀንሳል- ጥናት

በአንድ አንድ የዓለም ሀገራት ከምግብነት ባሻገር ሰዎች ከበሽታ ለማገገም ሲጠቀሙበት የነበረው ቃሪያ አሁን ላይ በወጣ ጥናት በልብ በሽታ እና በጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስ የመሞት አደጋን ይቀንሳል ተብሏል፡፡

ጥናቱ ቃሪያን የሚመገቡ እና የማይመገቡ 23 ሺህ ሰዎች የተሳተፉበት ሲሆን በተካሄደው ጥናት ቃሪያን የተመገቡት በልብ በሽታ እና በጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስ የመጠቃት አደጋን ቀንሶ ታይቷል፡፡

ከስምንት ዓመታት በላይ የተሳታፊዎች የጤና ሁኔታ እና የአመጋገብ ሁኔታ ክትትል የተደረገበት ሲሆን  ቃሪያን ቢያንስ በሳምንት አራት ጊዜ የሚመገቡ ሰዎች ከማይመገቡት አንፃር በልብ በሽታ እና በጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስ የመሞት እድላቸው 40 በመቶ ዝቅ ያለ መሆኑን አዲሱ ጥናት ያሳያል ፡፡

የጥናት ቡድኑ በቀጣይነት ቃሪያ ለጤና ጠቃሚ የሆነበትን የባዬ ኬሚካል ስርዓት ላይ የበለጠ ምርምር ለማድረግ አቅድ መያዙን ነው ያስታወቀው፡፡

ቃሪያን መመገብ  የሚኖረው ጠቀሜታን በተመለከተ ጥናቱ ያሳየው ውጤት ቃሪያ በሁሉም የአመጋገብ  ስርዓት ላይ እንዴት ጥቅም ላይ እየዋለ ነው የሚለውን ለማየት ያስችላል ብለዋል ተመራማሪዎቹ፡፡

ምንጭ፡- ሲ ኤን ኤን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.