Fana: At a Speed of Life!

ቅድሚያ ለሴቶች  የሩጫ  ውድድር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሴቶችን ብቻ የሚያሳትፈው ቅድሚያ ለሴቶች የሩጫ ውድድር ተካሄደ፡፡

በተሟላ ስርዓተ-ምግብ ምኞቷ ይሳካል በሚል መሪ ቃል ለ17ተኛ ጊዜ የተካሄደው ሩጫው 5ኪሎ ሜትር የሸፈነ ነው፡፡

ሴቶች ብቻ በተሳተፉበት በዚህ ሩጫ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በክብር እንግድት ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም ይህ ሩጫ ሴቶች መብታቸውን የሚስከብሩበት ነው ብለዋል፡፡

በዚህም ሴቶች መብታቸው፣ደህነታቸው፣እኩልነታቸው ተከብሮ የሚገባቸውን ድርሻ ሁሉ መውሰድ አለባቸው ብለዋል ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ፡፡

በዚህ ባለፈም በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ መገኘቱን በማስመልከት ቫየረሱን ባለበት ለማቆም መንግስት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪ ግን መመሪዎችን በመከተል እና ለመመሪዎቹ ተገዢ በመሆን እራሳችንን ከቫይረሱ እንጠብቅ በማለት አሳስበዋል፡፡

ሩጫው መነሻውን እና መድረሻውን አትላስ ሆቴል ያደረገ ሲሆን 15ሺህ የሚሆኑ ሴቶች ተሳትፈውበታል፡፡

5 ኪሎ ሜትር በሸፈነው ውድድር አትሌት ፅጌ ገብረ ሰላማ ውድድሩን ስታሸንፍ አትሌትያለምዘርፍ የኋላ እና ንግስት ሃፍቱ ሁለተኛ እና ሶስተኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቀዋል፡፡

በተምሳሌት ሴቶች ደግሞ ድምፃዊት ብሩክታዊት ጌታሁን(ቤቲ ጂ) ውድድሩን በአንደኝነት ስታጠናቅቅ ሲስተር አሳየች እና ኮሜዲያን ቤቲ ዋኖስ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ሆነው ውድድሩን አጠናቀዋል፡፡

ለአሸናፊዎችም አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ እና አትሌት መሰረት ደፋር ሽልማት አበርክተዋል፡፡

በፌቨን ቢሻው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.